በአጂያን ባህር የመሬት መንቀጥቀጥ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 116 ደረሰ
በፈረንጆቹ 1999 በተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ በቱርክ 18ሺ ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል
በቱርክ በመሬት መንቀጥቀጡ ከተጎዱና ከፈረሱ ህንጻዎች ስር የፍለጋና ህይወት አድን ስራ ተጠናቋል
በቱርክ በመሬት መንቀጥቀጡ ከተጎዱና ከፈረሱ ህንጻዎች ስር የፍለጋና ህይወት አድን ስራ ተጠናቋል
ቱርክ በአጂያን ባህር በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ ተከትሎ ከተደረመሱ ህንጻዎች ውስጥ የነፍስ አድንና የፍለጋ ስራውን ስትጨርስ፣ በመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት 116 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡
በአስር አመት ውስጥ ጠንካራ የተባለው የመሬት መንቀጥቀጥ በቱርኳ የወደብ ከተማ እዝመር 1035 ሰዎችን አቁስሏል፤ሌሎች 137 ሰዎች ደግሞ እየታከሙ እንደሚገኙ የቱርክ የአደጋና የድንገተኛ ጉዳይ ማኔጅመንት ባለስልጣን አስታውቋል፡፡
ባለስልጣኑ እንደገለጸው በተጎዱትና በተደረመሱት 17 ህንጻዎች የፍለጋና የነፍስ አድን ስራው መጠናቀቁን ገልጿል፡፡ በቱርክ በአደጋው114 ሰዎች የሞቱ ሲሆን ሁለቱ ደግሞ በግሪኳ ሳሞስ ደሴት በንዝረቱ ምክንያት ሞተዋል፡፡
ባለፈው ማክሰኞ የመሬት መንቀጥቀጡ ከተከሰተ ከ90 ሰአታት በኋላ የነፍስ አድን ሰራተኞች አንዲት ወጣት ሴት ከፍርስራሽ ውስጥ በህይወት ማውጣት ችለዋል፡፡ ባለስልጣኑ አንደገለጸው የአደጋ ሰለባ ለሆኑት ዜጎች 2790 ድንኳኖችንና ለጊዜያዊ መጠለያነት መሰራጨቱን አስታውቋል፤ከ10ሺ በላይ አልጋዎችም ተከፋፍለዋል ብለዋል፡፡
በአደጋው 22 ጀልባዎች ሰጥመዋል፤ሌሎች 43ዎች ከቦታው የተወሰዱ ሲሆን 40ዎቹን ማትረፍ መቻሉን ተነግሯል፡፡
በፈረንጆቹ 1999 በተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ በሰሜናዊ ምእራብ ቱርክ 18ሺ ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል፡፡ በአጂያን ባህር በቅርቡ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ 7.0 መጠን ያለው መሆኑ ተገልጿል፡፡