የ7ቤት አገው ፈረሰኞች 80 አመት ተከበረ
የ7 ቤት አገው ፈረሰኞች ማኅበር 80ኛ ዓመት ተከበረ
በበዓሉ ላይ የአገው ባሕላዊ አልባሳት፣ የመገልገያ ቁሳቁሶች፣ የባሕል ምግብ ዓይነቶች፣ የሀገረ-ሰቡ ትውን ጥበባት እና የፈረሰኞች ትርዒት ለታዳሚው ቀርቧል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንንና የባሕልና ቱሪዝም ሚንስትር ሒሩት ካሳውን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በበዓሉ ላይ ተገኝተዋል፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒሰትሩ "በታሪክ ፈረስ ወደኋላ ስንመለስ የአገው አባት አርበኞች የጠላት ወረራን ለመመከት አንድያ ሕይወታቸውን አስይዘውና ድል አድርገው ሲገቡ ፈረስ የትግሉም የድሉም ባለቤት ነበረ፣ የፈረስ ውለታ ከአባት አርበኞች ጋር ሲዘከር የሚውል ነው " ብለዋል።
በመሆኑም በዓሉ ከአድዋ ድል ጋር ከፍተኛ ትስስር ያለው ነው ብለዋል፡፡
የባሕልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶ/ር ሒሩት ካሳው በበኩላቸው "ፈረስ ለሥራ ወዳዱ የአዊ ሕዝብ ወደ ግንባር ወስዶ በድል የሚመለስ የጦር ሜዳ ባለሟል ብቻ ሳይሆን በሬን ተክቶ መሬት እየገመሰ አርሶ የሚያበላ ነው፣በሐዘን እና በደስታ ጊዜ ከአገው ማኅበረሰብ ዘንድ ከጎኑ የማይጠፋ ከፊት ቀድሞ የሚታይ ባለሟል ፈረስ ነው" ብለዋል።