በጎንደር በጥምቀት በዓል ላይ በደረሰ የመወጣጫ መደርመስ አደጋ የ10 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ፡፡
በጎንደር ከተማ አስተዳደር ዛሬ ጠዋት በጥምቀተ ባሕር ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን ሲከታተሉ የነበሩ ሰዎች ለመቀመጫነት የተሠራ ርብራብ እንጨት ተደርምሶ ድንገተኛ አደጋ አጋጥሟቸዋል፡፡
በጎንደር ከተማ ትናንት በተከበረው የጥምቀት በአል ላይ ከእንጨት የተሰራ መቀመጫ ተደርምሶ በደረሰው አደጋ የሟቾች ቁጥር 10 መድረሱን ፖሊስ አስታውቋል፡፡
በአደጋው ሌሎች 245 ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱም ተነግሯል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ኮማንደር አየልኝ ታክሎ ጥምቀተ ባህሩ በተዘጋጀበት ለእንግዶች መቀመጫ ተብለው ከተሰሩ አራት የእንጨት መቀመጫዎች መካከል አንዱ በከፍተኛ የሰው ብዛት ሳቢያ በመደርመሱ ጉዳቱ ሊደርስ ችሏል ብለዋል፡፡
ክስተቱ እንዴት ሊፈጠር እንደቻለ ተጠይቀው፣ ለበዓሉ ታዳሚዎች ተብሎ የተሠራው የእንጨት መቀመጫ ከአቅሙ በላይ በማስተናገዱ የተፈጠረ ችግር እንደሆነ ነው አቶ ተስፋ ያብራሩት፡፡
እንደ አቶ ተስፋ ገለጻ ከሆነ መቀመጫው ከ700 እስከ 1000 ጥሪ የተደረገላቸውን እንግዶች ያስተናግዳል ተብሎ ነበር የተሠራው፡፡ ነገር ግን በባሕረ ጥምቀቱ ይካሄድ የነበረውን ሃይማኖታዊ ሥርዓትና የበዓሉን ድባብ ለማየት በጉጉት ይጠባበቁ የነበሩ በርካታ ሰዎች በእንጨቱ ላይ በመውጣታቸው የተፈጠረ መደርመስ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ድርጊቱ ከመከሰቱ በፊት የፀጥታ ኃይሎች ሲከለክሉ እንደነበርም ጠቁመዋል፡፡
በዓሉን በሠላማዊ ሁኔታ ለማክበር የጎንደርና አካባቢው ወጣቶች ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በጋራ በመሆን ጥረት ሲያደርጉ መቆየታቸውንና ወጣቶች ላሳዩት በጎ ተግባር አመስግነዋል፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎችና የበዓሉ ታዳሚዎች በጉዳቱ የተደናገጡ ቢሆኑም ሁኔታው እንዲረጋጋ ላደረጉት አስተዋፅኦ ምሥጋና አቅርበዋል፡፡
ከተፈጠረው አደጋ ውጭ ምንም ዓይነት የፀጥታ ችግር እንልነበርና ታቦታቱ በሠላም ወደ አድባራቱ እንደገቡም ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ምንጭ፡- አብመድ