የጥምቀት ከተራ በዓል በመላው ኢትዮጵያ በድምቀት እየተከበረ ነው፡፡
በኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ በየዓመቱ ጥር 11 በድምቀት የሚከበረው የኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል ዛሬ በመላ ሀገሪቱ በድምቀት እየተከበረ ነው፡፡
በተለያዩ አካባቢዎች በርካታ የውጭና የሀገር ውስጥ ጎብኚዎች በተገኙበት ሀይማኖታዊ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ ነው በዓሉ እየተከበረ የሚገኘው፡፡ ትናንት በከተራ የጀመረው የበዓሉ አከባበር ነገም በቃና ዘገሊላ ይቀጥላል፡፡
በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የበአሉን አከባበር በፎቶ እናስቃኛችሁ፡፡ ፎቶዎቹ ከአል-ዐይን ኒውስ በተጨማሪ ከተለያዩ ሚዲያዎችም ያገኘናቸው ናቸው፡፡