በጦር ሜዳ ውሳኔ ሰጪነት ላይ ሮቦቶች የሰው ወታደራዊ አዛዥ ሚናን ሊተኩ ይችላሉ ተባለ
የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ሮቦቶች የሞት ሽረት ጉዳይ ያለምንም ማመንታት ፈጣን ውሳኔ ሊሰጡ ይችላሉ ተብሏል
ውሳኔ ሰጪነትን በሮቦቶች መተካት የታሰበው የሰው ልጆች አድልዎ አሊያም በስምምነት ውሳኔዎችን ሊያዘገዩ ስለሚችሉ ነው
ውጊያ እና ሌሎች ተልዕኮዎች በዘመናዊ የውትድርና ዘመቻዎች ውስብስብ ውሳኔዎች በፍጥነት እንዲደረጉ የሚጠይቁ ሲሆን፤ ይህንን ደግሞ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ሮቦቶች በቀላሉ ሊከውኑት ይችላሉ ተብሏል።
የአሜሪካው የመከላከያ ምርምር ፕሮጀክቶች ኤጀንሲ (ዲ.ኤ.አር.ፒ.ኤ) የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ሮቦቶች በውሳኔ ሰጪነት ሂደትን ለማስተዋወቅ ያለመ አዲስ ፐሮጀክት ይፋ ማድረጉን ዴይሊ ሜይል አስነብቧል።
ይህ የሆነበት ምክንያት፣ በገሃዱ ዓለም ድንገተኛ አደጋዎች ላ አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች ለመስማማት የሚቸገሩበት ውሳኔ አሰጣጥ ላይ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ሮቦቶች በቀላሉ ውሳኔ ሊሰጡ ስለሚችሉ ነው ተብሏል።
“ኢን ዘ ሙመንት” የሚል መጠሪያ ያለው አዲሱ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ስራ ውሳኔ ለመስጠት አስቸጋሪ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ አዲስ ቴክኖሎጂን ለማሳተፍ ያለመ መሆኑ ተነግሯል።
ወደ ወታደራዊ ሁኔታዎች ሲመጣም በጦርነቶች ላይ በሰዎች የተሳሳተ እና የዘገየ ውሳኔ ሰጪነት የሚደርሰውን የከፋ አደጋ ለመቀነስ የሚያስችል መሆኑን ኤጀንሲው አስታውቋል።
ምክንያቱም የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ሮቦቶች ያለውን መረጃ በፍጥነት በመተንተን ውሳኔ ላይ ለመስደረስ ስለሚያስቻላቸው ነው ተብሏል።
በዚህም ምክንያት ነው አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሮቦቶች በጦር ሜዳዎች የውሳኔ ሰጪነት ሚናን ከሰው ወታደራዊ አዛዦች ሊረከቡ ይችላ የተባለው።
አዲሱ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ሮቦቶች አሁን ላይ ገና የመጀመሪያ ደረጃ ላይ ናቸው የተባለ ሲሆን፤ በገሃዱ ዓለም ላይ ከመጠቀም በፊት ለማለማመድ ሁለት ዓመታት፤ ዝግጅት ደግሞ የ18 ወራት ጊዜ እንደሚያስፈልግም ተነግሯል።