“አውሬው” የሚል መጠሪያ የተሰጠው የሰሜን ኮሪያው ህዋሰኦንግ-17 ሚሳዔል
ሰሜን ኮሪያ የፈረንጆቹ 2022 ከገባ ወዲህ ከሃይፐርሶኒክ እስከ አህጉር አቋራጭ የተለያዩ ሚሳዔሎችን ሞክራለች
ከሰሜን ኮሪያ ሚሳዔሎች መካከል ህዋሰኦንግ-17 (አውሬው) ሚሳዔልን ምን የተለየ ያደርገዋል…?
ሰሜን ኮሪያ የፈረንጆቹ 2022 ከገባ ወዲህ ባለፉት ሶስት ወራ ውስጥ ከሃይፐርሶኒክ እስከ አህጉር አቋራጭ (አይ.ሲ.ቢ.ኤም) ሚሳዔሎች ሙከራ ማድረጓ ይታወሳል።
በቅርብ ቀናት ውስጥም የኒኩሌር የጦር መሳሪያን የታጠቀቸው ሰሜን ኮሪያ ከበርካታ የሚሳዔል ሙከራዎች መካከል ምንነቱ በውል ያልታወቀ መሳሪየ መተኮሷ ተሰምቷል።
የደቡብ ኮሪያ መከላከያ አዛዥ በሰጡት መግለጫም፤ ሰሜን ኮሪያ ምንነቱ ያልታወቀ መሳሪያ ወደ ምስራቃዊ የባህር ክልል አስወንጭፋለች ማለታቸው ይታወሳል።
ሰሜን ኮሪያ ለሙከራ ካስወነጨፈቻቸው ከሃይፐርሶኒክ እና አህጉር አቋራጭ (አይ.ሲ.ቢ.ኤም) ሚሳዔሎች መካከል “ህዋሰኦንግ-17 (አውሬው)” የሚል መጠሪያ የተሰጠው እንደሚገኝበትም ተነግሯል።
ህዋሰኦንግ-17 ሚሳዔል ምንድነው…?
ሰሜን ኮሪያ “ህዋሰኦንግ-17” ሚሳዔልን በፈረንጆቹ 2020 ባለካሄደችው ወታደራዊ ትርዒት ላይ በባለ 22 ጎማ ከባድ ተሸከርካሪ ላይ ጭና ለእይታ ማቅረቧ ይታወሳል።
የዘርፉ ባለሙያዎች “ህዋሰኦንግ-17” ሚሳዔልን “ግዙፉ” ወይም “አውሬው” ሲሉ የሚጠሩት ሲሆን፤ ሰሜን ኮሪያ ከዚህ ቀደም የነበራት “ህዋሰኦንግ-15” ላይ ቴክኒካዊ ማሻሻያዎች አድጋበት ነው ያቀረበችው ይላሉ።
ሚሳዔሉ አህጉር አቋራጭ (አይ.ሲ.ቢ.ኤም) ሚሳዔል አይነት ነው የተባለ ሲሆን፤ ሰሜን ኮሪያ ባሳለፍነው የካቲት እና አሁን ባለንበት መጋት ወር ላይ ለሙከራ ካስወነጨፈቻቸው መካከል እንደሚገኝ አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ አስታውቀዋል።
የኒኩሌር አረርን ጨምሮ የተለያዩ የጦር መሳሪየ አረሮች ተሸካሚ የሆነው “ህዋሰኦንግ-17” ለመመከት አስቸጋሪ ነው የተባለለት ሲሆን፤ “ህዋሰኦንግ-17” የመሳሪውን አቅም በቅርቡ ይፋ ታደርጋለች ተብሎ ይጠበቃል።
እንደ ባለሙያዎቹ ገለጻ ፒዮንግያንግ የሰሜን ኮሪያ መስራች እንደሆኑ የሚነገርላቸው የኪም ኢል ሱንግ ልደት ቀን ማለትም የፊታችን ሚያዚያ 7 “ህዋሰኦንግ-17” ሚሳዔልን ልታስወንጭፍ ትችላለች።