አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ በሰው ልጅ ላይ የመጥፋት ስጋት ደቅኗል ተባለ
ይህ የባለሙያዎች ማስጠንቂያ የታተመው መቀመጫዉን አሜሪካ ባደረገው 'ሴንተር ሮር ኤአይ' ድረ ገጽ ላይ ነው
አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ የሚያመጣው አደጋ ከወረርሽን እና ከኑክሌር ጦርነት አይተናነስም ብሏል ቡድኑ
የሰው ሰራሽ አስተውሎት ወይም አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ በሰው ልጅ የመኖር ህልውና ላይ ስጋት መደቀኑን ባለሙያዎች እና ታዋቂ ነጋዴዎች እየገለጹ ነው።
ይህ የነጋዴ እና የባለሙያ ቡድን አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ የሚያመጣውን ጣጣ ያስጠነቀቁ ሲሆን የሰው ልጅን ሊያጠፋ የሚችል ስለሆነ አለምአቀፍ ትብብር ያስፈልጋል ብለዋል።
አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ የሚያመጣው አደጋ ከወረርሽን እና ከኑክሌር ጦርነት አይተናነስም ብሏል ቡድኑ።
ይህ የባለሙያዎች ማስጠንቂያ የታተመው መቀመጫዉን አሜሪካ ባደረገው 'ሴንተር ሮር ኤአይ' ድረ ገጽ ላይ ነው።
ማስጠንቀቂያው የቻትጂቲፒ ፈጣሪ የሆነውን ሳም አልትማንን እና የአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ ባለቤት አባት የሚባለውን ጄፍ ሂንተንንም ያካትታል።
ቀደም ሲል ሂንተን ለኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ በአርቴፊሻል ኢንሊጀንስ ዘርፍ የሚደረግ ማዘመን ለማህበረሰብ እና ለሰው ልጅ የከፋ አደጋ ይዞ ይመጣል ሲል ተናግሮ ነበር።
ባለፈው መጋቢት ቢሊየነሩን ኢሎን መስክን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ አለም አቀፍ ባለሙያዎች በዚህ ጉዳይ መክረው ነበር።
የአሜሪካው ሳም አልትማን አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ በአለም ላይ ከባድ ጉዳት እንደሚያስከትል ቢገልጽም፣ በሰው ሀብት ዘርፍ መሰረታዊ ለውጥ የሚመጣ ነው ይላል።