በፎቶ እድሜ የሚናገረው አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ
የኒውዮርክ ተመራማሪዎች ራሳችን በራሳችን በምናነሳው ፎቶ እድሜያችን የሚገምት ሰው ሰራሽ አስተውሎት አስተዋውቀዋል
ሰው ሰራሽ አስተውሎቱ በስድስት መመዘኛዎች እድሜን ይገምታል ተብሏል
የሰው ሰራሽ አስተውሎት ወይም አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የሰው ልጅን ስራ እያቀለለ ይገኛል።
በሚሊየኖች የሚቆጠሩ የሰው ልጆችን ስራ የመንጠቅ እድሉም ሰፊ ነው መባሉ ስጋት ከፈጠረ ዋል አደር ብሏል።
የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች እንደ ሰው ልጅ አስበው ፈጣን ምላሽ የሚስጡ የሰው ሰራሽ አስተውሎቶችን ማበልጸግ ላይ ተጠምደው ፉክክሩም ቀጥሏል።
የኒውዮርክ ተመራማሪዎችም ራሳችን በራሳችን በምናነሳው ፎቶ (ሰልፊ) እድሜያችን የሚገምት ሰው ሰራሽ አስተውሎት አስተዋውቀዋል።
ሰው ሰራሽ አስተውሎቱ በአይን እና ቆዳ ላይ በሚታዩ ስድስት ምልክቶች አማካኝነት እድሜን ይገምታል ተብሏል።
የ39 አመቷ የዴይሊሜል ድረገጽ ሰራተኛ በዚሁ ሰው ሰራሽ አስተውሎት ፎቶዋን አስገብታ እድሜዋን እንዲገምት አድርጋለች።
ውጤቱም በ40ዎቹ መጀመሪያ እንደምትገኝ ማመላከቱ “ቀኔን አበላሽቶት ውሏል” ብላለች።
አርቲፊሻል ኢንተለጀንሱ የፊትን ገጽታ በመቃኘት እድሜን መገመቱ ራስን ለመመልከት ወሳኝ ነው ይላል ኖቮስ የተሰኘው ከእድሜ ጋር የተያያዙ ምርምሮችን የሚያደርገው ተቋም።
ምክንያቱ ደግሞ የፊት ገጽታ የሰውነት ማርጀትን ያመላክታልና ነው።
አልኮል፣ ሲጋራ ማጨስ እና ሌሎች አጉል ልማዶች የፊት ቆዳን በመለወጥ ወጣቶችን ያለእድሜያቸው የትልቅ ሰው መልክ ይሰጣሉ።
የኖቮስ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስም ወጣቶች ፎቷቸውን አስገብተው በሚያገኙት የእድሜ ግምት መሰረት ራሳቸውን እንዲመለከቱና ሱስ ውስጥ ያሉትም ከመጥፎ ልማዶች እንዲወጡ ሊያነቃ እንደሚችል ተገልጿል።
በሰልፊ ፎቶዎ እድሜዎን ለማወቅ ይህን ሊንክ ይጫኑ