ልዩልዩ
ለአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ከፍተኛ በጀት የመደቡ ሀገራት
ሀገራት የሰው ልጅን ስራ ያቀላል ለሚሉት አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በየአመቱ በቢሊየን ዶላር ይመድባሉ
ቴክኖሎጂው በየጊዜው እያደገና ፉክክሩም እየተጠናከረ ቢሄድም ከፍ ያሉ ስጋቶችም ተደቅነውበታል
አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (ሰው ሰራሽ አስተውሎት) የሰው ልጆችን ህይወት ለማቅለል የሚያስችል ቴክኖሎጂ ነው።
ቋንቋ የሚተርጉሙ፣ መረጃ የሚተነትኑ፣ ንግግርን ወደ ጽሁፍ የሚለውጡና ለየትኛውም ጥያቄ ምላሽ መስጠት የሚችሉ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን የሚጠቀሙ መተግበሪያዎች እየተበራከቱ ነው።
በቅርቡ የወጣ ጥናት አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ 300 ሚሊየን የሰው ልጆች ሊሰሯቸው የሚችሉ ስራዎችን ተክተው መስራት እንደሚችሉ አመላክቷል።
ስጋቱን እንረዳለን ግን ከጉዳቱ ጥቅሙ ያመዝናል ያሉ ሀገራትም ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ በዘርፉ ላይ እየሰሩ ይገኛሉ።