ሀገራት ልማት እና የአየር ንብረት ለውጥን ለምን ያቃርኑታል?
አል አይን - ሞሀሙድ ሞሄልዲን (ዶ/ር)
የአየር ንብረት ጥበቃ ስራን ከካርበን ልቀት ጋር ብቻ የማያያዝ ችግር በአንዳንድ ሀገራት በስፋት ይታያል። የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን እንጂ ችግሩን ለመቅረፍ የሚወሰዱ እርምጃዎች የዘላቂ እና አካታች እድገት መሰረት መሆናቸውንም ይዘነጉታል።
ዘላቂ ልማትን ከአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ስራ ጋር የማቃረን ልማድ በተለያዩ ሀገራት መንግስታት ይታያል።
የአለማችን ፈተና የሆኑ ጉዳዮችን ከመፍታትና እድሎችን ከመጠቀም ይልቅ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖዎችን እያነሱ ትልቅ መደበቂያ አጀንዳ እያደረጉት ነው።
የዘላቂ ልማት እሳቤን የመዘንጋትና የአየር ንብረት ለውጥን ከፈጣን ልማት ጋር የማያያዙ ልማድ ያልለቀቃቸው ሀገራት መንግስታት ቁጥርም ቀላል አይደለም።
የአየር ንብረት ለውጥን የካርበን ልቀትን ከመቀነስ ጋር ብቻ የማያያዝ ጉዳዩን የማሳነሱ ችግር አሁንም ጎልቶ የሚታይ ነው።
የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን እንጂ ችግሩን ለመቅረፍ የሚወሰዱ እርምጃዎች የዘላቂ እና አካታች እድገት መሰረት መሆኑ ይዘነጋል።
የካርበን ልቀት በከባቢ አየር ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት የማጉላታቸውን ያህል ልቀትን ለመቀነስ የገቡትን ቃል ግን ሲፈፅሙ አለመታየቱም ለዚህ ማሳያ ነው።
197 ሀገራት በፈረንሳይ ፓሪስ በ2015 ስምምነት ሲፈራረሙ የበካይ ጋዝ ልቀትን ለመቀነስ ብቻ ሳይሆን ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ ለመገንባት ቃል ገብተው ነበር።
በ2030 የበካይ ጋዝ ልቀትን በ45 በመቶ ለመቀነስ የያዙት የገቡት ቃልም ከመቀኘስ ይልቅ በ15 በመቶ እየጨመረ ነው።
በካዬቹ ሀገራት የካርበን ልቀትን መቀነስ ላይ ልናተኩር ይገባል እያሉ ቢደሰኩሩም የሚታይ ለውጥ አላመጡም።
በአንፃሩ ታዳጊ እና በከባቢ አየር ብክለት ዝቅተኛ ድርሻ ያላቸው ሃገራት በአየር ንብረት ለውጥ ከፍተኛ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ እያስተናገዱ ነው።
የበለፀጉት ሀገራት በፓሪሱ ስምምነት ቃል ገብተው ያልፈፀሙት የካርበን ልቀትን የመቀነስ ጉዳይ ብቻ አይደለም።
አለም የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ጦርነት ቢያውጅም አስቀድሞ ጦርነቱን በሚያስቀሩና ጉዳቱን የሚከላከሉ ጋሻዎችን በማበጀት ረገድ ደካማ ነው።
በግብፅ ሻርም አልሼክ በተካሄደው ጉባኤ የተቀመጡ የውሃ አስተዳደር፣ ዘላቂ ግብርና እና የምግብ ስርአት መገንባት እንዲሁም የደን ጭፍጨፋ እና ውሃማ አካላት ላይ የተጋረጡ አደጋዎችን መቀነስ ትኩረት ቢሰጣቸውም አፈፃፀማቸው አናሳ ነው።
በታዳሽ ሃይል ልማት ረገድም ከፋይናንስ እጥረት እና ሌሎች ችግሮች ጋር በተያያዘ በፓሪስም ሆነ ሻርም አል ሼክ በተገባው ቃል መሰረት አልተሄደበትም።
የአየር ንብረት ለውጥ መቀነሻ ዘዴዎችን ከዘላቂ ልማት እቅዶች ጋር አሰናስሎ መተግበር ካልተቻለ አለማችን ከገባችበት አጣብቂኝ መውጣት ይከብዳታል።
ዘላቂ ልማት እና የአየር ንብረትን ለመጠበቅ የሚወሰዱ እርምጃዎች እርስ በርስ ተመጋጋቢ መሆናቸው መዘንጋት የለበትም።
የአየር ንብረት ለውጥን ተፅዕኖ ደጋግሞ ከማውራትና የማይፈፀም ቃል ከመግባት ይልቅ ከባቢ አየርን የሚጠብቁ እና ልማትን የሚያበረታታቱ እቅዶችን አውጥቶ ወደ ስራ መግባት ያስፈልጋል።