አረብ ኢምሬትስ ካራካል የተሰኘ የኤርባስ ስሪት ሂልኮፕተሮችን ተረከበች
የተባበሩት አረብ ኢምሬት ፕሬዝዳንት መሀመድ ቢን ዛይድ ፈረንሳይን በመጎብኘት ላይ ናቸው
አረብ ኢምሬትስ ከፈረንሳይ 80 ራፋሌ የጦር አውሮፕላኖችን ለመግዛት የ14 ቢሊየን ዩሮ ውል መፈራረሟ ይታወሳል
አረብ ኢምሬትስ ካራካት ወይም ኤች225ኤም የተሰኘውን የኤርባስ አቪዬሽን ኩባንያ ስሪት የሆኑ ሂልኮፕተሮችን ገዝታለች።
የሂልኮፕተር ግዢው ስምምነት የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ባሳለፍነው ታህሳስ ወር አቡዳቢን በጎበኙበት ወቅት ከአረብ ኢምሬት ፕሬዚዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ ጋር የተፈጸመ ነበር።
በስምምነቱ መሰረት አረብ ኢምሬት ለ12 ካራካል ሂልኮፕተር ግዥ 800 ሚሊዮን ዩሮ ለኤርባስ እንደምትከፍል ተገልጿል።
ኤርባስ በስምምነቱ መሰረትም ከአንድ ወር በፊት የመጀመሪያውን ሂልኮፕተር ለተባበሩት አረብ ኢምሬት ማስረከቡን አስታውቋል።
ይህ ሂልኮፕተር የአስቸኳይ ጊዜ ተልዕኮዎችን በፍጥነት እና በብቃት ለመከወን የሚረዳ ዘመናዊ የአቪዬሽን ምርት ነው ተብሎለታል።
አረብ ኢምሬት ከዚህ በፊት 80 ራፋኤል ኤፍ 4 የተሰኘውን የጦር አውሮፕላን ከፈረንሳይ ለመግዛት ተመሳሳይ ስምምነት ማድረጓ አይዘነጋም።
አረብ ኢምሬትስ እና ፈረንሳይ በየጊዜው ዲፕሎማሲያዊ እና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነታቸውን በማጠናከር ላይ ሲሆኑ ወደ ፓሪስ ያቀኑት ፕሬዝዳንት መሀመድ ቢን ዛይድ ከፈረንሳይ አቻቸው ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በሁለትዮሽ፣ አካባቢያዊ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ ይጠበቃል።
በአረብ ኢምሬትስ ከፍተኛ መሪ ታሪክ ፈረንሳይን በመጎብኝት በፈረንጆቹ 1991 ላይ ሼክ ዛይድ ፓሪስን ጎብኝተዋል።
የወቅቱ የአረብ ኢምሬት ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ ወደ ፈረንሳይ ሲያቀኑ ከ32 ዓመት በኋላ ፓሪስን የጎበኙ መሪ ሆነዋል።