ፖለቲካ
የአረብ ኢሚሬትስ ፕሬዝዳንት የፈረንሳይ ይፋዊ የስራ ጉብኝታቸውን ጀመሩ
ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ በፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን አቀባበል ተደርጎላቸዋል
አረብ ኢሚሬትስና ፈረንሳይ በኢነርጂና በትራንስፖርት መስኮች እንደሚፈራራሙ ይጠበቃል
የአረብ ኢሚሬትስ ፕሬዝዳንት መሀመድ ቢን ዛይድ የፈረንሳይ ይፋዊ የስራ ጉብኝታቸውን በይፋ ጀምረዋል።
በትናንትናው ለት ምሽት ፈረንሳይ ፓሪስ የደረሱት ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ ዛሬ በፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑዔል ማክሮን በኤሊሴ ቤተ መንግስት ይፋዊ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።0
ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ በኤሊሴ ቤተመንግስት ከፈረንሳይ አቻቸው ኢማኑኤል ማክሮን ጋር ተገናኝተው ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ሌሎች የፈረንሳይ ባለስልጣናትን ያነጋግራ።
ሼህ መሀመድ ቢን ዛይድ አልነሃያን በፈረንሳይ ቆይታቸው በኢነርጅ እና በትራንስፖርት መስኮች እንደሚፈራራሙ ኤኤፍፒ ዘግቧል፡፡
የፈረንሳዩ ጉብኝት ፕሬዝዳንቱ ስልጣን ከያዙ በኋላ ያደረጉት የመጀመሪያ አለምአቀፍ ጉብኝት ነው፡፡