የተሳፋሪዎቹን ኪሎ መመዘን እጀምራለሁ ያለው አየር መንገድ ምን ገጠመው?
“ፊንኤይር” አየር መንገድ ተሳፋሪዎቹን “በእጅ ከያዙት ሻንጣ ጋር አንድ ላይ መመዘን ጀምራለሁ” ብሏል
ከበድ ያለ ኪሎ ያላቸው ሰዎች “ተጨማሪ ሊያስከፍለን ነው” በሚል ስጋት እየተቃወሙት ነው
የፊንላንድ አየር መንገድ የሆነው “ፊንኤይር” ተሳፋሪዎቹን በእጅ ከያዙት ሻንጣ ጋር አንድ ላይ መመዘን እንደሚጀምር አስታውቋል።
አየር መንገዱ “ተሳፋሪዎቹን እና በእጅ የሚይዙትን ቦርሳ የምመዝነው በበረራ ወቅት ትክክለኛ የአውሮፕላኑን ክብደት ለማወቅ ነው” ቢልም ከአሁኑ ተቃውሞዎችን እያስተናገደ ነው።
አወዛጋቢው ውሳኔውን ያሳለፈው “ፊንኤይር” አየር መንገድ ባሳለፍነው ሳምንት ሰኞ ከሄልሲሰንኪ የሚነሱ ሳታፈሪዎች ላይ ሙከራ መጀመሩን አስታውቋል።
እስካሁንም 500 በጎ ድቃደኛ መንገደኞች በተመዝነው ይሳፈሩ ዘመቻው መሳተፋቸውን የፊንኤይር ቃል አቀባይ ካይሳ ቲካኔን ተናግረዋል።
አየር መንገዱ በሰጠው መግለጫ “ተሳፋሪ መመዘን ያስፈለገው የአውሮፕላን ክብደት ለማመጣጠን እና ደህንነቱ የተጠበቀ በረራ ለማድረግ ነው” ብሏል።
ሆኖም ግን በርከት ያሉ የማህበራዊ ተስስር ተጠቃሚዎች በአየር መንገዱ ውሳኔ ላይ የተለያየ አስተተያየት እየሰጡ ሲሆን፤ በዚህም ገሚሱ ሲቃወመው፤ ቀሪዎቹ ደግሞ ከልክ ያለፈ ውፍረትን ለመከላከል ጥሩ ውሳኔ ነው ሲሉ አሞካሽተውታል።
ውሳኔውን የተቃወሙ መንገደኞች በአየር መንገዱ ውሳኔ መደንገጣቸውን እና መበሳጨታቸውን በመግለጽ ላይ ይገኛሉ።
የአየር መንገዱ እርምጃ ኪሏው ከበድ ያለ እና ከመጠን በላይ የሆነ የሰውነት ውፍረት ያላቸውን ሰዎች የሚያሸማቅቅ እና ጭካኔ የተሞላበት ነው ሲሉም ገልጸውታል።
በተለይም ኪሏቸው ከበድ ያሉ እና ከልክ ያለፈ ውፍረት ያላቸው ሰዎች በሰውነታቸው ክብደት መሸማቀቅ እንደማይፈልጉ እና በአየር መንገዱ መሳፈር እንደሚያቆሙ ገልጸዋል።
አንዳንዶቸ ደግሞ “አየር መንገዱ በሰዎች ኪሎ መጠን ጭማሪ ክፍያ ሊቀበል ነው” ሲሉም ውሳኔውን ተቃውመዋል።
ባሳለፍነው ዓመት ነኃሴ ወር ላይ የኮሪያ ግዙፍ አየር መንገደግ ኮሪያን ኤይር የተሳፋሪዎቹን ኪሎ መመዘን እንደሚጀመር በመግለጽ፤ ይህንንም የሚያድገው ትክክለኛ የአውሮፕላኑን ክብደት ለማወቅ እና ትክክለኛውን የአውሮፕላኑን ክብት ለማቀው እንደሆነም አስታውቆ ነበር።
በዚሁ ሰሞን ከአንድ ወር ቀደም ብሎ ኢዚ ጄት አውሮፕላኑ ከመጠን በላይ ከመመዘኑ ጋር ተያይዞ 19 መንገደኞችን ከአውሮፕላን እንዲወርዱ ማድረጉም ይታወሳል።