የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመቀሌ ስላጋጠመው አደጋ ምን አለ?
በተሳፋሪዎና የበረራ ቡድን አባላት ላይ ምንም አይነት ጉዳት አለመድረሱ ተገልጿል
አየርመንገዱ በአሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፊያ የተከሰተውን አደጋ መንስኤ በዝርዝር እየመረመርኩ ነው ብሏል
መነሻውን አዲስ አበባ ያደረገው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በመቀሌ ሊያርፍ ሲል አደጋ ገጠመው።
የበረራ ቁጥሩ ኢቲ106 የሆነው ቦምባርዲየር ኪው 400 አውሮፕላን ጎማው ላይ በተፈጠረ ችግር ማኮብኮቢያ አስፋልቱን ስቶ ወጥቷል።
በአሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ከቀኑ 8 ስአት አካባቢ በተከሰተው መጠነኛ አደጋ ሁሉም ተሳፋሪዎችና የበረራ ቡድን አባላት ጉዳት ሳይደርስባቸው በሰላም መውጣታቸውንም አየርመንገዱ ባወጣው መግለጫ ጠቁሟል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመቀሌ የተከሰተውን አደጋ መንስኤ በዝርዝር እየመረመረ መሆኑን አስታውቋል።
በተፈጠረው ችግር መጉላላት ለደረሰባቸው መንገደኞችም ይቅርታ ጠይቋል።