በርካታ አየር መንገዶች የመካከለኛው ምስራቅ የአየር ክልልን መጠቀም ማቆማቸውን አስታወቁ
ወደ እስራኤል የሚያደርጉትን በረራ ያቆሙ አየር መንገዶች በርከት ብለዋል
እስራኤል በሰዓታት ልዩነት ውስጥ የሃማስና የሄዝቦላህ አመራሮችን በመግደሏ ውጥረት ነግሷል
በመካከለኛው ምስራቅ እንደ አዲስ ውጥረት መንገሱን ተከትሎ በርካታ አየር መንገዶች በበአየር ክልሉ በኩል የሚያደርጉትን በረራ ማቆማቸው አታውቀዋል።
በተጨማሪም በርከት ያሉ አየር መንገዶች ወደ እስራኤል የሚያደርጉትን በረራ ማቆማቸውን እንዳስታወቁ ሮይተርስ ዘግቧል።
አየር መንገዶቹ የመካከለኛው ምስራቅ የአየር ክልልን መጠቀም ያቆሙት እስራኤል በሰዓታት ልዩነት ውስጥ ሁለት ከፍተኛ የሃስና የሄዝቦላ አመራሮች መግደሏን ተከትሎ በነገሰው ውጥረት ነው።
የሲንጋፖር አየር መንገድ ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ የኢራን እና የሊባኖስ አየር ክልሎችን በመተው ሌላ አማራጭ የአየር ክልሎችን መጠቀም መጀመሩን ያስታወቀ ሲሆን፤ ለዚህ ምክንያቱ ለደህንነተ ቅደሚያ ስለምስጥ ነው ብሏል።
የታይዋን ኢቫ ኤር እና የቻይና አየር መንገዶችም ወደ አምስተርዳም ለሚያደርጉት በረራ በኢራን አየር ክልል በኩል መጠቀም ማቆማቸውን አስታውቀዋል።
ባሳለፍነው ሚያዚያ ወር ለይ ኢራን በእስራኤል ላይ የከፈተችውን መጠነ ሰፊ ጥቃት ተከትሎ በርካታ የአሜሪካ እና የአውሮፓ ሀገራት አየር መንዶች የመካከለኛው ምስራቅ የአየር ክልችን መጠቀም መቆማቸው ይታወሳል።
በሰዓታት ልዩነት ውስጥ የሂዝቦላ እና የሀማስ ከፍተኛ አመራሮች ግድያን ተከትሎ ሊኖር የሚችለው የአጸፋ ምላሽ ቀጠናዊ ግጭትን ሊቀሰቀስ እንደሚችል ተሰግቷል።
ኢራን የሀማስ የፖለቲካ ቢሮ ሀላፊ እስማኤል ሀኒየህ በዋና ከተማዋ ቴህራን በተፈጸመባቸው የሚሳኤል ጥቃት መገደላቸው ተከትሎ በእስራኤል ላይ ከፍተኛ የበቀል እርምጃ እንደምትወስድ ዝታለች፡፡
የተባሩት መንግስታ ጸጥታው ምክር ቤት የአመራሮቹን ግድያ ተከትሎ ሂዝቦላ እና ኢራን በእስራኤል ላይ የአጸፋ ጥቃት የሚሰነዝሩ ከሆነ ነገሮች ከቁጥጥር ውጭ ሊሆኑ እንደሚችል አስጠንቅቋል፡፡