ዋሽንግተንን መገደብ በመካከለኛው ምስራቅ የአሜሪካን ውድቀት ያሳያል ተባለ
አረብ ኤምሬትስ አሜሪካ የኢራን ኢላማዎችን ለመምታት ወታደራዊ ተቋሞቿን እንዳትጠቀም ገደብ አስቀምጣለች
የአረብ ኢምሬትስ ውሳኔ እውነተኛ ዲፕሎማሲን የተከተለና ለቀጠናዊ መረጋጋት ቅድሚያ የሰጠ ነው ተብሏል
ዋሽንግተንን መገደብ በመካከለኛው ምስራቅ የአሜሪካን ውድቀት እንደሚያሳይ የዘርፉ ባለሙያዎች ለአል ዐይን ኒውስ ተናግረዋል።
አረብ ኤምሬትስ አሜሪካ የኢራን ኢላማዎችን ለመምታት በግዛቷ የሚገኙ ወታደራዊ ተቋሞቿን እንዳትጠቀም ገድባለች የተባለ ሲሆን፤ ይህ የአረብ ኢምሬትስ ውሳኔ እውነተኛ ዲፕሎማሲን የተከተለና ለቀጠናዊ መረጋጋት ቅድሚያ የሰጠ ነው ብለዋል።
አሜሪካ አሁን እየተከተለቸው ያለው አካሄድ የአሜሪካን የፖሊሲ ውድቀት ወደ ውጭ በማላከክ፤ የጨዋታውን ኳስ ወደ አጓሮቿ እና ወዳጅ ሀገራት ሜዳ ላይ የመጫወት ስራ እየሰራች መሆኑንም ነው ባለሙያዎች የተነጋሩት።
የአሜሪካው ፖሊሪኮ ጋዜጣ በስም ያልጠቀሳቸውን አራት የአሜሪካ ባለስልጣናትን ጠቅሶ ባወጣው ዘገባው ላይ፤ አረብ ኢምሬትስን ጨምሮ የተወሰኑ የአረብ ሀገራት አሜሪካ በሀገራ ውስጥ ያለውን ወታደራዊ መገልገያ ተጠቅማ በኢራን እና አጋሮቿ ላይ ጥቃት እንዳትሰነዝር ክለከላ እየጣሉ መሆኑን ጠቅሷል።
ተንታኞች የፖሊቲኮ ዘገባን እንዴት ተመለከቱት?
በተንታኞች እይታ በፖሊቲኮ ዘገባ ውስጥ የተካተቱት መግለጫዎች በመካከለኛው ምስራቅ አካባቢ የአሜሪካን ውድቀት ያሳየ እና አሜሪካ የጨዋታውን ኳስ አረብ ኡምሬትስን ጨምሮ በአጓሮቿ እና ወዳጅ ሀገራት ሜዳ ላይ ለመጫወት እንደሆነ ያላክታል ብለዋል።
ተንታኞቹ በአስተያየታቸው፤ የአሜሪካ አስተዳደር መጀመሪያ ላይ በመካከለኛው ምስራቅ ያጋጠመውን ውድቀት አቅጣጫ በመቀየር ለገበያ ለማቅረብ እንደሞከረ ጠቁመዋል።
ነገር ግን በአካባቢው የተከሰቱት ተከታታይ ለውጦች ዋሽንግተን ሌሎችን ለመወንጀል እንድትሞክር ያነሳሷቸውን ክፍተቶችን ማሳየቱን ገልጸዋል።
ዶ/ር አብዱል ካህሌቅ አብደላ ከጉዳዩ ላይ ከአል ዐይን ኒውስ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ አረብ ኢምሬትስ ውሳኔ ከአሜሪካ ጋር ያላትን ግንኙት ሊያሰፋ ይችላል ያሉ ሲሆን፤ “ይህ የሚሆነው ከዋሽንግተን ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ጉዳዮች የተለየ ከሆነ ወይም የአሜሪካ አስተዳደር ቅር የማይለው ከሆነ ነው" ብለዋል።
የአረብ ኢምሬትሱ ተንታኝ አክለውም፤ “አሜሪካ በዚህ ውሳኔ ቅር የምትሰኝ ከሆነ አቋሟ ያስከተለውን ውጤት እና በክልሉ ውስጥ ያሉትን በርካታ ስህተቶች መሸከም አለባት” ሲሉም ተናግረዋል።
በመቀጠልም "ከኢራንም ሆነ ከታጣቂዎቿ ጋር ግንባር አንከፍትም” ያሉት ተንታኙ፤ ምክንያቱም “አሜሪካ ከኢራን ጋር ጦርነት የሚከፈትበት ጊዜ እንደደረሰ ታምናለች" ብለዋል።
የፖለቲኮ ዜናን በተመለከተም ዶ/ር አብዱል ካህሌቅ አብደላ፤ እንዲህ ያሉ ዜናዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚወጡት አንዳንድ ሀገራትን ለመጫን ወይም ቅሬታ ለመግለጽ ላይ ነው” ሲሉ ገልጸዋል።
ምእራባውያን ምናልባት እንዲህ ዓይነቱ አፈትልከው የወጡ መረጃዎችን በመጠቀም ሁኔታውን ለመለወጥ ሊሰሩ እንደሚችሉ ያሳወቁት ዶ/ር አብዱል ካህሌቅ አብደላ፤ የባህረ ሰላጤው አገሮች ይህ አስቀድሞ ማወቅ አለባው ብለዋል።
"የግራ መጋባት ሁኔታ"
የቀድሞ የኢሚሬትስ ዲፕሎማት ዩሱፍ አል ሀሰን አሁን ካለው ጊዜ ጋር አያይዘው የአሜሪካ ያለውን የምርጫ ድባብ ያነሱ ሲሆን፤ ዋሽንግነት በዚህ የምርጫ “በጣም ግራ መጋባት” ስራዎች ይሰራሉ ብለዋል።
አል ሀሰን ለአል አይን ኒውስ እንደተናገሩት፤ አየሜሪካ ፖለቲካ ስርዓት ውስጥ ቁለፉ ነገር የሆነው የምርጫ ጉዳይ ነው ያሉ ሲሆን፤ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሁሌም አስተዳዳሪው አካል ይጎዳል፤ ከዚህ ጋር ተያይዞም ከዴሞክራቶች እና ሪፐብሊካን ጋር ተያየዞ በርካታ ግራ አጋቢ ነገሮች ይከሰታሉ ብለዋል።
ዩሱፍ አል ሀሰን በመቀጠል፣ “እንዲህ ባለ ውስብስብ በሆነ ሁኔታ ውስጥ የአረብ ኢሚሬትስ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ አለመግባባቶችን ለመፍታት፣ ግጭቶችን ለመፍታት እንዲሁም ቀውሶችን እና ችግሮችን ለማስወገድ የሚወስደውን እያንዳንዱን እርምጃ ማጤን አለበት” ሲሉም ገልጸዋል።
አሜሪካ ያላት ሁለት አማራጮች…
ሳሚር ሳልሃ እዚህ ላይ ሁለት ጥያቄዎች የሚያነሱ ሲሆን፤ ይህም አሜሪካ በእስራኤል ላይ ጫና ለመፍጠር የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ማስጠንቀቂያ ትወስድ ይሆን? ወይስ ዋሽንግተን ባለችበት ሆና ፖሊሲዋን በዚህ መንገድ ለማስቀጠል ትሞክራለች? የሚሉ ናቸው።
ከነዚህ ጥያቄዎች አንፃር፣ የዓለም አቀፍ ግንኙነት ፕሮፌሰሩ ሳሚር ሳልሃ ዋሽንግተን አጋሮቿ የሚናገሩትን ማዳመጥ እና ይህንን ዘዴ መገምገም አለባት ያሉ ሲሆን፤ አሊያም የሚመጡ ሸክም እና ውጤታቸውን መሸከም አለባት ብለዋል።