በኮረና ቫይረስ ምክንያት በረራ ያቆሙ አየር መንገዶች
በኮረና ቫይረስ ምክንያት በረራ ያቋረጡ አየር መንገዶች
በቻይና በተከሰተውና እስከ ሀሙስ ድረስ 170 ሰዎችን በገደለው የኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በርካታ አየር መንገዶች ወደ ቻይና የሚያደርጉትን በረራ ማቋረጣቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ቫይረሱ አስከ አሁን 8000 ሰዎችን ማጥቃቱ ተነግሯል፡፡
በራራ ያቋረጡ አይር መንገዶች የሚከቱለት ናቸው፡፡
የካናዳ አየር መንገድ
የካናዳ አየር መንገድ ከባለፈው ማክሰኞ ጀምሮ ወደ ቻይና የሚደረጉ የተመረጡ በረራዎችን ሰርዟል፡፡
ኤየር ፍራንስ
ኤየር ፍራንስ ከትናንት ጀምሮ ወደ ቻይና የሚደረጉና ከቻይና ወደ ፈረንሳይ የሚደረጉ ሁሉንም በረራዎች ከአንድ ሳምንት በላይ ለሆነ ጊዜ አቋርጧል፡፡
ኤየር ኢንዲያ
ኤየር ኢንዲያም ሙምባይ-ድልሂ-ሻንዳ የሚያደርገውን በረራ ለሁለት ሳምንት ለሚጠጋ ጊዜ አቋርጧል፡፡
ኤየር ሲኦል
ኤየር ሲኦል ከማክሰኞ ጀምሮ ሁሉንም በረራዎች ሰርዟል፡፡
ኤየር ታናዛኒያ
ኤየር ታናዘኒያ የመንገደኞች በረራን እንደሚስተላላፍና፣የቻርተር በረራዎችን ወደ የካቲት እንደሚያዛውር አስታውቋል፡፡
አሜሪካ ኤርለይንስ
ትልቁ የአሜሪካ አየር መንገድ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ከሎስአንጀለስ ወደ ቤጂንግና ሻንጋይ የሚያደርገውን በራራ ያቋርጣል፡፡
የእንግሊዝ አየር መንገድ
የእንግሊዝ አየር መንገድ ወደ ቻይና የሚደርገውን በረራ ለአንድ ወር አቆማለሁ ብሏል፡፡
ከነዚህ አየር መንገዶች በተጨማሪ የካዚይ ፓስፊክ፣ የዴልታ አየር፣ የግብፅ፤ የኬንያ፣ የፊንኤየር፣ ላዮን አየር፣ የሉፍታንዛ፣ የሳስ፣ የተርኪሽ፣ የዩናይትድ፤ የዩናይትድ ፓስፊክና የቨርጂን አትላንቲክ አየር መንገዶች በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በረራቸውን አቋርጠዋል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግን ወደ ቻይና የሚደርገውን በረራ አላቋረጥኩም ብሏል፡፡