በጦርነቱ እስካሁን በእስራኤል 900 ሰዎች የሞቱ ሲሆን በጋዛ በኩል ደግሞ 700 ሰዎች ተገድለዋል
ከሀማሰ ጥቃት በኋላ በርካታ አየር መንገዶች ወደ እስራኤል የሚያደርጉትን በረራ አግደዋል።
የፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ሀማስ ከአራት ቀናት በፊት በእስራኤል ላይ ያልተጠበቀ ጥቃት ማድረሱን ተከትሎ በርካታ አየር መንገዶች ወደ ቴል አቪቭ የሚያደርጉትን ጉዞ አግደዋል።
በግጭቱ ምክንያት በመቶዎች የሚቆጠሩ በረራዎች ተስተጓጉለዋል።
የሀማስን ጥቃት ተከትሎ እስራኤል በሀማስ መቀመጫ በሆነችው ጋዛ ላይ ከባድ የአየር ጥቃት እያደረሰች ነው፤ጋዛን በመክበብ ጥቃት አድራሾችንም ለመግደል ወስናለች።
እስራኤል ጋዛን ለመክበብ በምታደርገው ጥረት በደቡባዊ እስራኤል ከፍተኛ ጦር አሰማርታለች።
እስካሁን በጦርነቱ በእስራኤል 900 ሰዎች የሞቱ ሲሆን በጋዛ በኩል ደግሞ 700 ሰዎች ተገድለዋል።