ጦሩ ከሰኞ ጀምሮ ምንም አይነት አዲስ የሰርጎ መግባት እንቅስቃሴ አለመኖሩን አስታውቋል
እስራኤል የጋዛ ድንበርን መልሳ መቆጣጠሯን እና የሀማስ ታጣቂዎች ሰብረው በገቡበት ድንበር ፈንጂ እያጠመደች እንደሆነ ተናግራለች።
- እስራኤል የምትሰጠው ምላሽ "መካከለኛው ምስራቅን ይቀይራል"- ጠቅላይ ሚኒስትር ንታንያሁ
- እስራኤልና ፍልስጤም ከ30 አመት በፊት የተፈራረሙት የኦስሎ ስምምነት ምን ይላል?
ሀገሪቱ ድንበሩን ተቆጣጠርኩ ያለችው ያላባራውን የአየር ድብደባ ካደረገች በኋላ ነው።
ሀገሪቱ ይህን ያለችው ሀማስ እስራኤል የፍልስጤም ከተሞችን ያለማስጠንቀቂያ በቦምብ የምትደበድብ ከሆነ የያዛቸውን እንደሚገድል ከዛተ በኋላ ነው።
የእስራኤል ጦር ከዚህ በፊት ታይቶ የማያውቅ 300 ሽህ ተጠባባቂዎችን በመጥራት በጋዛ ሰርጥ ላይ እግድ ጥሏል።
ከአንድ ሽህ 500 በላይ ህይወት የቀጠፈው ይህ ግጭቱ፤ ለእስራኤል ዓለም አቀፍ ድጋፍ እንድታገኝ ረድቷታል።
ፍልስጤምን በመደገፍ የጎዳና ላይ ተቃውሞዎች የተደረጉም ሲሆን፤ ጦርነቱ እንዲቆምና ሲቪሎች ጥበቃ እንዲደረግላቸው ተማጽነዋል።
የእስራኤል የቴሌቭዥን ጣቢያዎች እንደዘገቡት በሀማስ ጥቃት 900 እስራኤላውያን ሲገደሉ 600 የሚሆኑት ደግሞ ቆስለዋል።
በደርዘን የሚቆጠሩት ደግሞ በሀማስ መታገታቸውን ሚዲያዎቹ ዘግበዋል።
ከእስራኤል ሟቾች መካከል የሙዚቃ ፊስቲቫል ላይ የተገደሉት 260 ሰዎች አብዛኞቹ ወጣቶች ናቸው ተብሏል።
የእስራኤል ጦር ከሰኞ ጀምሮ ምንም አይነት አዲስ የጋዛ ሰርጎ መግባት አለመኖሩን ተናግረዋል።