በወር አራት ሺህ ዩሮ ገቢ የምታስገባው ሰው ሰራሽ ሞዴል
ኤታና ሎፔዝ የተሰኘችው የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሞዴል በአራት ወራት ውስጥ 110 ሺህ ተከታዮችን አፍርታለች
እውነተኛ ሞዴሎች ዋጋ ማሻቀብን ተከትሎ የተሰራችው ህች ሞዴል በስፔን ኩባንያ ተሰርታለች ተብሏል
በወር አራት ሺህ ዩሮ ገቢ የምታስገባው ሰው ሰራሽ ሞዴል….
እውነተኛ የሰው ልጅ ሞዴሎችን ተጠቅሞ ማስታወቂያዎችን መስራት ከጊዜ ወደ ጊዜ ዋጋቸው እየተወደደ መምጣቱን ተከትሎ ሰው ሰራሽ ሞዴሎች ምርጫ እየሆኑ መጥተዋል፡፡
የስፔኑ ክሉለስ የተሰኘው የቴክኖሎጂ ኩባንያ አርቲፊሻል ቴክኖሎጂ ወይም ሰው ሰራሽ አስተውሎትን በመጠቀም የበይነ መረብ ሞዴሎችን ፈጥሯል፡፡
ይህ ኩባንያ ኤታና ሎፔዝ የተሰኘችውን ሰው ሰራሽ ሞዴል በመስራት ከአራት ወራት በፊት ነበር ለገበያ ያስተዋወቃት፡፡
ይህች የበይነ መረብ ወይም ድጅታል ሞዴል ልክ እንደሰው የኢንስታግራም ገጽ ያላት ሲሆን በጥቂት ወራት ውስጥም 110 ሺህ ተከታዮችን ማፍራት ችላለች፡፡
በየጊዜው ፎቶዎቿን እና ተንቃሰቃሽ ምስሎቿን ለተከታዮቿ የምታጋራው ይህች ሰው ሰራሽ ሞዴል በኩባንያዎች እና የንግድ ሰዎች ምርቶቻቸውን ለማስተዋወቅ ተመራጪ እንደሆነች ተገልጿል፡፡
የለንደን ኬሚስቶች አርቲፊሻል አልኮል መስራታቸውን ገለጹ
የሞዴሏ ባለቤት ክሉለስ ኩባንያም በየወሩ በአማካኝ አራት ሺህ ዩሮ ገቢ እያገኘ እንደሆነ አስታውቋል፡፡ ኤታና ሎፔዝ ያላት የሰውነት ቅርጽ፣ የጸጉር ቀለም እና ሌሎች እውነተኛ ሰው የሚያስመስላትን ነገሮች ማድረጓ ተወዳጅ እንድትሆን አድርጓታል ተብሏል፡፡
እውነተኛ የሰው ልል ሞዴሎችን ተጠቅሞ ምርቶችን ማስተዋወቅ በዋጋ ምክንት ውድ በመሆኑ እንደ ኤታና ሎፔዝ ያሉ ሰው ሰራሽ ሞዴሎች እየተወደዱ መምጣታቸውን ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል፡፡
ዋና መቀመጫውን ስፔን ባርሴሎና ያደረገው ክሉለስ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ተጨማሪ ሞዴሎችን በመስራት ለደንበኞች የሚሰጠውን አገልግሎት የማስፋት እቅድ እንዳለው አስታውቋል፡፡
በርካታ የዓለማችን የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች አርቲፊሻል ቴክኖሎጂ ወይም ሰው ሰራሽ አስተውሎት ቀስ በቀስ የሰው ልጆችን እየተካ እና የህልውና አደጋ ሊደቅን ይችላል ሲሉ ማስጠንቀቃቸው ይታወሳል፡፡
የበለጸጉ ሀገራትም በአርቲፊሻል ቴክኖሎጂ ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ማድረግ የሚያስችላቸውን ፖሊሲ በማዘጋጀት ላይ ሲሆኑ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎችን በማማከር ላይም ናቸው፡፡