አል ዐይን ኒውስ ለዱባይ ኤክስፖ 2020 ሙሉ ሽፋን ለመስጠት ዝግጅቱን አጠናቋል
ዱባይ ኤክስፖ 2020 ሁነቶች ብቻ የሚቀርቡብት "Expo Dubai 2020" በሚል ልዩ ድረ ገጽም አዘጋጅቷል
በኤክስፖው ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ የ192 ሀገራት የሚሳተፉ ሲሆን፤ ከ25 ሚልየን በላይ ጎብኚዎች እንሚጎበኙትም ይጠበቃል
አል ዐይን ኒውስ ከሁለት ቀናት በኋላ ለሚጀመረው ግዙፉ የዱባይ ኤክስፖ 2020 ሙሉ ሽፋን ለመስጠት ዝግጅቱን አጠናቋል።
የዱባይ ኤክስፖ 2020 በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች አስተናጋጅነት ከሁለት ቀናት በኋላ ማለትም መስከረም 21 ቀን 2014 በይፋ የሚከፈት ሲሆን፤ እስከ መጋቢት 22 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ለ6 ወራት የሚካሄድ ይሆናል።
የዱባይ ኤክስፖ 2020 ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ የ192 ሀገራት እንደሚሳተፉበት የሚጠበቅ ሲሆን፤ ከ25 ሚልየን በላይ ጎብኚዎች እንደሚጎበኙትም ይጠበቃል።
አል ዐይን ኒውስም ይህንን ግዙፍ ዓለም አቀፍ ኤክስፖ በተለየ መልኩ ሰፊ ሽፋን ለመስጠት አስፈላጊውን ዝግጅት ያጠናቀቀ ሲሆን፤ ተከታዮቻችን ስፍራው ላይ እንዳሉ እስኪሰማቸው ድረስ እና ስለ ኤክስፖው በቂ ግንዛቤን እንዲያገኙ እና ለጉብኝት እንዲያቅዱ የሚያደርጉ ልዩ የዜና እና የመዝናኛ ይዘቶችን የሚያቀርብ ይሆናል።
እንዲሁም ሁሉም ሰው የዱባይ 2020 ኤክስፖ ክስተቶችን በቅጽበት እና በሚያስደስት ተሞክሮ እንዲከታተል በልዩ የይዘት ቴክኒኮች አማካኝነት የሚያቀርብ መሆኑንም ይገልጻል።
ለዚህም አል ዐይን ኒውስ ልዩ የሽፋን እቅድ ያዘጋጀ ሲሆን፤ የሽፋን ዕቅዱ በይዘት ውስጥ ካለው የመሪነት ሚና እንዲሁም ዘላቂነት ባለው የልማት ፖሊሊው መሰረት ዲጂታል እና አሳታፊ ይዘቶችን በመጠቀም የተከታዮቹን ፍላጎት የሚያማሉ አሳታፊ እና አዝናኝ ዜናዎችን ለማድረስ ነው።
አል ዐይን ኒውስ ዱባይ ኤክስፖ 2020 ሁነቶች ብቻ የሚቀርቡብት ልዩ ድረ ገጽም ያዘጋጀ ሲሆን ድረ ገጹም "Expo Dubai 2020" በሚል ዩዘር ስም ማግኘት ይቻላል።
ድረ ገጹ በውስጡ በርካታ ክፍሎችን የያዘ ሲሆን፤ ኤክስፖውን በተመለከተ ከሰዎች ለሚቀርቡ ማንኛውም ጥያቄዎች በኤሌክትሮኒክስ እና በሰው ሀይል በመታገዝ ምላሽ የሚሰጥ ክፍልም በድረ ገጹ ውስጥ ይገኛል።
በተጨማሪም በማህበራዊ ትስስር ድረ ገጽ አማካኝነት መረጃዎችን ተደራሽ ለማድረግ ልዩ የሆነ የትዊተር ገጽ የከፈተ ሲሆን፤ የቀጥታ ስርጭቶችን ጨምሮ ኤክስፖውን የተመለከቱ የተለያዩ መረጃዎችን ወደ ተከታዮቹ የሚያደርስ ይሆናል።
አል ዐይን ኒውስ የዱባይ ኤክስፖ 2020 ሽፋኑን ከአረብኛ ቋንቋ በተጨማሪ በአማርኛ፣ በፈረንሳይኛ፣ በተርኪሽ እና በፋርስ ቋንቋዎች በተለያዩ የኣለም ክፍል ለሚገኙ ተከታዮቹ የሚያቀርብ መሆኑንም ያስታውቃል።
የአል ዐይን ኒውስ ዋና አዘጋጅ አህመድ ሰይድ አል አላዊ፤ ዩ.ኤ.ኢ ከኮሮና ወረርሽኝ በኋላ እንዲህ አይነት ዓለም አቀፍ ሁነት ማዘጋጇ ትልቅ ስኬት ነው ብለዋል።
አል ዐይን ኒውስም ይህንን ግዙፍ እና ዓለም አቀፍ ሁነት የሆነውን የዱባይ ኤክስፖ 2020 ለመሸፈን ልዩ እቅድ አዘጋጅቶ እየሰራ ነው ሲሉም ተናረዋል።
ከኮሮና ቫይረስ መስፋፋት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘጋጀውን ይህንን ግዙፍ ዓለም አቀፍ ኤክስፖ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ እና አሳታፊ የሆነ የዲጂታል ፕላት ፎርሞችን ተጠቅሞ ከዚህ ቀደም ባልተለመደ መልኩ ለህብረተሰቡ ያቀርባም ብለዋል።