ኢትዮጽያን ጨምሮ የ192 ሀገራት ለሚሳተፉበት የዱባይ ኤክስፖ 2020 ዝግጅት እየተደረገ ነዉ
ኢትዮጽያ lዱባይ ኤክስፖ 2020 ከወዲሁ ሰፊ ዝግጅት በማድረግ ላይ ነች:: ለዝግጅቱም የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ 1.5 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ያደረገች ሲሆን ኤክስፖው የሚቀርብበት አዳራሽ እየተገነባ ነዉ፡፡ የዱባይ 2020 ኤክስፖ ከጥቅምት እስከ መጋቢት 2013 ዓ.ም. ለስድስት ወራት የሚካሄድ ይሆናል።
የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋናው አረጋ ኢትዮጵያ በይፋ ኤክስፖ ላይ እንደምትሳተፍ ባበሰሩበት ወቅት እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ በኤክስፖው ላይ ለሚኖራት ተሳትፎ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ ነው ብለዋል።
በዚህ ኤክስፖ ላይ ከ190 በላይ ሀገራት የሚሳተፉበት ሲሆን ከ25 ሚልየን በላይ ጎብኚዎች እንደሚጎበኙትም ይጠበቃል፡፡ ኢትዮጽያም በዝግጅቱ ላይ (the land of origions) የሚል ርዕስ የተሰጠዉ አዉደ ርዕይ እንደምታካሂድም ሚኒስትር ዴኤታዉ ተናግረዋል፡፡ በኤክስፖው ኢትዮያ የግ በግብርና፣ ጨርቃጨርቅ፣ ቆዳና የቆዳ ውጤቶች፣ ማእድን እንዲሁም በአይሲቲ እና ሌሎች መስኮች ያላትን እምቅ አቅም ታስተዋውቃለች፡፡
ለዚሁ ጉዳይ የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ ላደረገችው የገንዘብ ድጋፍ ሚኒስትር ዴኤታው ምስጋናቸውንም አቅርበዋል፡፡
የዱባይ ኤክስፖ 2020 ከፍተኛ አማካሪ ሙሳ አል-ሀሽም በበኩላቸዉ ይህ ኤክስፖ አለምን ለሁሉም የተሻለ ለማድረግ በትብብር መንፈስ አገራትን በማሰባሰብ ባለፉት 168 ዓመታት በዓለም ከተካሄዱት ምርጥ እክስፖዎች አንዱ ነዉ ብለዋል፡፡
ዱባይ ኤክስፖ 2020 የዱባይና የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች ብቻ ሳይሆን መካከለኛ ምስራቅን ጨምሮ የአፍሪካና ደቡብ ኤሲያ ሀገራትንም እንደሚያካትት አማካሪዉ ተናግረዋል፡፡ የአለማችንን 3 ቢሊዮን ህዝብ በሚይዙት በነዚህ ሀገራት መሰል ኤክስፖ ተደርጎ እንደማያውቅም ሙሳ አል-ሀሽም አብራርተዋል፡፡
ኢትዮጵያን ጨምሮ የአፍሪካ ሀገራት በተለያዩ መስኮች ያላቸውን እምቅ አቅም ለዓለም ማህበረሰብ በሰፊው ለማስተዋወቅ ኤክስፖው ሰፊ እድል እንደሚፈጥርላቸውም ጠቅሰዋል፡፡