በዱባይ ኤክስፖ የኢትዮጵያን ኢንቨስትመንት፣ንግድና ቱሪዝም ለማስተዋወቅ እየተሰራ ነው-ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር
በኮቪድ 19 ሳቢያ የተራዘመው የዱባይ 2020 ኤክስፖ ከመስከረም 21፣ 2014 ጀምሮ ይካሄዳል
በዱባይ 2020 ኤክስፖ ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ 192 ሀገራት የሚሳተፉበት ሲሆን ከ25 ሚሊዮን በላይ ጎብኚዎች ይጠበቃሉ
በዱባይ ኤክስፖ የኢትዮጵያን ኢንቨስትመንት፣ ንግድና ቱሪዝም ለማስተዋወቅ እየተሰራ መሆኑን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ።
በኮቪድ 19 ሳቢያ የተራዘመው የዱባይ 2020 ኤክስፖ ከመስከረም 21 2014 ጀምሮ እንደሚካሄድ የወጣለት መርሃ ግብር ያመለክታል።በኤክስፖው ላይም ኢትዮጵያን በተለያየ መልኩ ለማስተዋወቅ ሰፊ እድል የሚፈጥር መሆኑን ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በፌስ ቡክ ገጹ ባወጣው መረጃ አመላክቷል
በኤክስፖው ላይ ኢትዮጵያን የሚገልጹ ሙዚቃዎች፤ ባህሎች እና የተለያዩ ሀገራችንን የሚያስታውሱ ቀኖች ተሰይመው የሚከበሩ መሆኑንም ሚኒስቴሩ አስታውቋ።
የቡና፣ የንግድ፣ የኢንቨስትመንት፣የብሄራዊ ክብረ-በዓል ቀናቶች እንደሚከበሩ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የወጪ ንግድ ማስፋፊያ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ ገልጸዋል።
የዱባይ 2020 ኤክስፖ ከጥቅምት እስከ መጋቢት 2013 ዓ.ም ለስድስት ወራት እንደሚካሄድ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረ ቢሆንም፤ በዓለም ላይ በተከሰተው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ሳቢያ መራዘሙም ይታወሳል።
በተራዘመው መርሃ ግብር መሰረትም የዱባይ ኤክስፖ 2020 መክፈቻ ስነ ስርዓት እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር መስከረም 20 2021 የሚካሄድ ሲሆን፤ ኤክስፖውም ለ6 ወራት ቀጥሎ የሚሄድ ይሆናል።
በኤክስፖው ከተሳትፎ የቀረቡት ሶስት ንዑስ ክፍሎች መካከል ዕድል፣ ተንቀሳቃሽነት እና ዘላቂነት የሚሉ ይገኙበታል።
ባህልና ቅርሶችን፤ ኢንቨስትመንትን፣ ንግድና ቱሪዝምን በማስተዋወቅ ከፍተኛ ሚና የምኖረው የኤክስፖው ንዑስ ክፍል ዕድል በመሆኑ ኢትዮጵያም በዚህኛው የኤክስፖው ንዑስ ክፍል የምትካፈል መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል።
“ምድረ ቀደምት እና እድሎች” በሚል መሪ ቃል ኢትዮጵያ በመሳተፍ በዋናነት ዳያስፖራውን፣ የግሉን ዘርፍ፣ እንዲሁም ክልሎችን እና የባህል አምባሳደሮችን በማካተት የኢትዮጵያን ኢንቨስትመንት፣ ንግድና ቱሪዝም ለማስተዋወቅ እየሰራነውም ብለዋል።
የዱባይ ኤክስፖ 2020 ላይ ኢትዮጽያን ጨምሮ የ192 ሀገራት እንደሚሳተፉበት የሚጠበቅ ሲሆን፤ ከ25 ሚልየን በላይ ጎብኚዎች እንደሚጎበኙትም ይጠበቃል።
የዱባይ 2020 ኤክስፖ ከጥቅምት እስከ መጋቢት 2013 ዓ.ም ለስድስት ወራት እንደሚካሄድ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረ ቢሆንም፤ በዓለም ላይ በተከሰተው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ሳቢያ መራዘሙም ይታወሳል።
በአረብ ሀገራት ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሚካሄድ ለተነገረለት የዱባይ ኤክስፖ 2020 ከ10 ዓመት በላይ ፈጀ ዝግጅት ሲደረግ ቆይቷል።