አል አይን በፍጻሜው ጨዋታ የጃፓኑ ዮኮሃማ ኤፍ ማሪኖስ 5ለ1 አሸንፏል
የአረብ ኤምሬትሱ የእግር ኳስ ክለብ አል አይን የ2024 የእስያ ሻምፒዮንስ ሊግ ሻምፒዮን በመሆን ዋጫውን አንስቷል።
በአርጀንቲናዊው ሄርናን ክሬስፖ የሚሰለጥነው አል አይን በፍጻሜው ጨዋታ የጃፓኑ ዮኮሃማ ኤፍ ማሪኖስ በሜዳው ያስተናገደ ሲሆን፤ ጨዋታውንም 5ለ1 በሆነ ሰፊ ልዩነት አሸንፏል።
በዚህም በጃፓን በተካሄደው ጨዋታ ላይ 2ለ1 ተሸንፎ የነበረው አል አይን በሜዳው ውጤቱን በመቀልበስ በደርሶ መልስ ጨዋታ ድምር ውጤት 6ለ3 በመርታት የእስያ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ ማንሳት የቻለው።
በሃዛ ቢን ዛይድ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ላይም ሶፊን ራሂሚ እና ኮጆ ላባ ለአል አይን እያንዳንዳቸው ሁለት ግቦችን ከመረብ ያሳረፉ ሲሆን፤ አሌሃንድሮ ሮሜሮ አንድ ግብ ከመረብ አሳፍሯል።
የጃፓኑ ዮኮሃማ ኤፍ ማሪኖስን ከመሸነፍ ያልታደገችው ብቻኛ ግብ ያን ማቴአስ ከመረብ አሳርፏል።
ይህንን ተከትሎም አል አይን ከ20 ሺህ በላይ ደጋዎቹ በተገኙበት ሃዛ ቢን ዛይድ ስታዲየም የ2024 የእስያ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫውን አንስቷል።
የ2024 የእስያ ሻምፒዮንስ ሊግ ሻምፒዮን አል አይን ከዚህ ቀደም በፈረንጆቹ 2003 ላይም የእስያ ሻምፒዮንስ ሊግ ሻፒየን መሆኑ ይታወሳል።