የስፔኑ ሪያል ማድሪድ የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን 14 ጊዜ በማንሳት ቀዳሚው ነው
በአለማቀፍ ደረጃ በአህጉራዊ የክለቦች ውድድር እንደ አውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ተወዳጅነትን ያተረፈ የለም።
ጅማሮውን በ1955 ያደረገውና እስከ 1992 ድረስ የአውሮፓ ዋንጫ በሚል ስያሜ ሲካሄድ የቆየው ውድድር የአውሮፓ ሃያላን ክለቦችን የሚያፋጥጥ በመሆኑ አለማቀፍ ትኩረትን እንዲያገኝ አድርጎታል።
ውድድሩ ከተጀመረበት 1955 አንስቶ 14 ጊዜ ሻምፒዮን የሆነው የስፔኑ ሪያል ማድሪድ የአውሮፓን ግዙፉን ዋንጫ ደጋግሞ በማንሳት የሚስተካከለው አልተገኘም።
የጣሊያኑ ኤሲ ሚላን ሰባት ጊዜ የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን በማንሳት ይከተላል።
የጀርመኑ ባየርሙኒክ እና የእንግሊዙ ሊቨርፑል እኩል ስድስት ጊዜ ዋንጫውን ያነሱ ሲሆን፥ የሪያል ማድሪድ ተቀናቃኝ ባርሴሎና አምስት ጊዜ ዋንጫውን ወደ ካታላን ወስዷል።
ቼልሲ፣ ጁቬንቱስ፣ ፖርቶ፣ ኖቲንግሃም ፎረስት፣ ቤነፊካ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ ሁለት ጊዜ የወሰዱ ሲሆን፥ የ2022/23 ሻምፒዮኑ ማንቸስተር ሲቲ ዋንጫውን ያነሳ ስድስተኛው የእንግሊዝ ክለብ ሆኗል።
የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን 23 ክለቦች ያነሱ ሲሆን ደጋግመው ያነሱትን 10 ክለቦች ይመልከቱ፦