የሱዳኑ መሪ አልቡርሃን ከግድያ ሙከራ ማምለጣቸው ተነገረ
አልቡርሃን የወታደሮችን የምረቃ ሰነ ስርአት እየተከታተሉ በነበረበት ወቅት በምስራቅ ሱዳን የሚገኘው የጃቢት ካምፕ በድሮን ተመትቷል ተብሏል
የሱዳን ጦር ቃል አቀባይ የምረቃት ስነ ሰርአት በሚካሄድበት ቦታ ሁለት ጥቃቶች መፈጸማቸውን ተናግሯል
የሱዳኑ መሪ አልቡርሃን ከግድያ ሙከራ ማምለጣቸው ተነገረ።
የሱዳን የሉአላዊ ምክርቤት ሊቀመንበር እና የሱዳን ጦር አዛዥ የሆኑት ጀነራል አል ቡርሃን በምስራቅ ሱዳን ከተፈጸመባቸው የድሮን ጥቃት ማምለጣቸውን የሱዳን ሚዲያዎች በዛሬው አለት ዘግበዋል።
አልቡርሃን የወታደሮችን የምረቃ ሰነ ስርአት እየተከታተሉ በነበረበት ወቅት በምስራቅ ሱዳን የሚገኘው የጃቢት ካምፕ በድሮን ተመትቷል ተብሏል።
ምንጮች እንደገለጹት ከሆነ አል ቡርሃን የደረሰባቸው ጉዳት የለም። ከአል ቡርሃን ጋር ከነበሩት ውስጥ የተጎዱ አሉ ተብሏል።
አልቡርሃን የሚሊታሪ ኮሌጁን 68ኛ ዙር እና የአየር ኮሌጅ እና ናቫል አካዳሚን 20ኛ እና 23ኛ ዙር ወታደሮችን ምርቃት በሬዲሲ ግዛት ጃቢት በሚገኘው የእግረኛ ጦር ኢንስቲትዩት ስቴዲየም እየተከታተሉ ነበር።
የሱዳን ጦር ቃል አቀባይ የምረቃት ስነ ሰርአት በሚካሄድበት ቦታ ሁለት ጥቃቶች መፈጸማቸውን ተናግሯል።
በሱዳን፣ በጀኔራል አልቡርሃን በሚመሩት የሱዳን ጦር እና ጀነራል መሀመድ ሀምዳን ደጋሎ ወይም ሄሜቲ በሚመሩት የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ጦር መካከል ባለፈው ሚያዝያ ወር የተጀመረው ጦርነት አሁንም እንደቀጠለ ነው።
በጦርነቱ ሳቢያ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሲገደሉ ከ10 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ደግሞ ተፈናቅለዋል።