የግብጹ ፕሬዝደንት አል ሲሲ በፍልስጤም እጣፈንታ ጉዳይ ምን አሉ?
እስራኤል በጋዛ የምታደርገው ወታደራዊ ዘመቻ ካበቃ በኋላ የአረብ ኃይል የጋዛ ሰረጥ ጸጥታ ያስከብር የሚለውን ሀሳብ የአረብ ሀገራት አልተቀበሉትም
አል ሲሲ ምስራቅ እየሩሳሌምን ዋና ከተማ አድርጎ የፍልስጤም ሀገር እንዲመሰረት በ1967 የተደረሰው ስምምነት አልተሳካም ብለዋል
የግብጹ ፕሬዝደንት አል ሲሲ ፍልስጤም ከወታደራዊ እንቅስቃሴ ነጻ ቀጣና ልትሆን ትላለች የሚል ሀሳብ ሰንዝረዋል።
ፕሬዝደንት አቡዱል ፈታህ አል ሲሲ እንደተናገሩት ለፍልስጤምም ሆነ ለእስራኤል የደህንነት ዋስትና ለመስጠት፣ በፍልስጤም በጊዜያዊነት አለምአቀፍ ሰላም አስከባሪ ሊገባ እና ከወታደራዊ እንቅስቃሴ ነጻ ቀጠና ልትሆን ትችላለች።
"ፍልስጤም ከወታደራዊ እንቅስቃሴ ነጻ እንድትሆን በእኛ በኩል ዝግጁ ነን። ለሁለቱም መንግስታት የሚሆን መፍትሄ እስከሚመጣ የአሜሪካ፣ የተመድ፣ የአረብ ወይም የኔቶ ኃይል ሰላም ማስከበር ይችላሉ" ብለዋል ሲሲ።
ሲሲ ይህን ያሉት ከስፔን ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቸዝ እና ከቤልጄም ጠቅላይ ሚኒስትር አሌክሳንደር ዲ ካሮ ጋር በካይሮ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው።
አል ሲሲ ምስራቅ እየሩሳሌምን ዋና ከተማ አድርጎ የፍልስጤም ሀገር እንዲመሰረት በ1967 የተደረሰው ስምምነት አልተሳካም ብለዋል።
እስራኤል በጋዛ የምታደርገው ወታደራዊ ዘመቻ ካበቃ በኋላ የአረብ ኃይል የጋዛ ሰረጥ ጸጥታ ያስከብር የሚለውን ሀሳብ የአረብ ሀገራት አልተቀበሉትም።
የጆርዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አይማን ሳፋዲ የአረብ ሀገራት በእስራኤል ጥቃት ወደ ወደመችው ጋዞ መሄድ እንደማይፈልጉ ተናግረዋል።
የሀማስ ይዞታ በሆነችው ጋዛ ላይ መጠነ ሰፊ ወታደራዊ ዘመቻ እያካሄደች ያለችው እስራኤል ሀማስን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት አቅዳለች።
እስራኤል ሀማስ ስጋት የማይሆንበት ደረጃ ከደረሰ በኋላ ጋዛን ወርራ እንደማትቆይ መግለጿ ይታወሳል።