ዳይሬክተሯ ተጨማሪ 1200 ህጻናት በቦምብ በፈራረሱ ህንጻዎች ስር እንደተቀበሩ ይታመናል ብለዋል
ጋዛ በዓለም ላይ ለህጻናት "እጅግ አደገኛ ቦታ" ነው ተባለ ።
ጋዛ በዓለም ላይ ለህጻናት እጅግ አደገኛ ቦታ ነው ሲል የተመድ የህጻናት ፈንድ(ዩኒሴፍ) ገለጸ።
የዩኒሴፍ ዋና ዳይሬክተር ካትሪን ሩሴል የእስራኤል እና ሀማስ ጦርነት ከተቀሰቀሰበት ከባለፈው ጥቅምት ወር ጀምሮ 5300 ህጻናት መገደላቸውን ለተመድ የጸጥታው ምክርቤት አስረድተዋል።
ዳሬክተሯ እንደገለጹት የህጻናት ሞት ከጠቅላላው ሞት 40 በመቶ ይሸፍናል።
ከጋዛ ጉብኝት የተመለሱት ዳይሬክተሯ ሁኔታው ያልተጠበቀ እና ያዩት ነገር እንደሚረብሻቸው ተናግረዋል።
ሩሴል በሀማስ እና በእስራኤል መካከል ተኩስን ጋብ ለማድረግ እና ተጋቾችን ለመልቀቅ ባለፈው ሮብዕ የተደረሰውን ስምምነት በበጎ ተቀብለውታል።
ሀማስ ባለፈው ጥቅምት የእስራኤልን ድንበር በመጣስ ጥቃት በፈጸመት ጊዜ 1200 ሰዎችን ገድሎ፣ 240 የሚሆኑትን ደግሞ አግቶ መውሰዱ ይታወሳል።
ነገርግን ሩሴል ለተፈጠረው ቀውስ እልባት ለመስጥ ተኩሱ ጋብ ከማድረግ ባሻገር ተኩስ አቁም አስለፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።
ዳይሬክተሯ ተጨማሪ 1200 ህጻናት በቦምብ በፈራረሱ ህንጻዎች ስር እንደተቀበሩ ይታመናል ብለዋል።
ተመድ እና በርካታ ሀገራት እስራኤል በጋዛ የምታደርገውን ጥቃት እንድታቆም ቢጠይቁም፣ ሀማስን ለማጥፋት እቅድ የያዘችው እስራኤል ጦርነቱን የጋብ የማድረግ እንጅ ማቆም እንደማትፈልግ ገልጽ አድርጋለች