ሆስፒታሎች ኢላማ መሆናቸው ቀጥሏል፤ በጋዛ የሚገኘው ግዙፉ የኢንዶኔዢያ ሆስፐታል ተደብድቧል
ሃማስ በእስራኤል ላይ ድንገተኛ እና ያለተጠበቀ ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ የተቀሰቀሰው ጦርነት ዛሬ 45ኛ ቀኑን ያስቆጠረ ሲሆን፣ አሁንም እንደቀጠለ ነው።
እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ የምታደርሰው ጥቃት ተጠናክሮ ቀጥሏል፣ እስራኤል ጦር አዳሩን በጋዛ ኢንዶኔዢያ ሆስፒታል ላይ ጥቃት ሰንዝረለች።
በጥቃቱም 12 ሰዎች የሞቱ ሲሆን፤ የሆስፒታሉ ዋነኛ የቀዶ ጥገና ህክምና ክፍል እና ሌሎችመ ዋነኛ ክፍሎች በደረሰባቸው ጉዳት ስራ አቁመዋል፤ የእስራኤል ታንኮች ወደ ሆስፒታሉ እየተቃረቡ ነወ።
እስራኤል በአል ሺፋ ሆስፒታል ስር 55 ሜትር የሚረዝም ዋሻ ማግኘቷ የሚያሳይ ቪዲዮ የለቀቀች ሲሆን፤ የሆስፒታሉ አስተዳዳሪዎች ስለ ዋሻ የሚነገረው ውሸት ነው ብለዋል።
ታጋቾችን የማስለቀቅ ድርድር
ሃማስ 200 የእስራኤልና የሌሎች ሀገራት ዜጎችን እስካን አግቶ የሚገኝ ሲሆን፤ ኳታርን ጨምሮ ሌሎች ሀገራት ታጋቾችን ለማስለቀቅ እያደራደሩ ይገኛሉ።
በትናትናው እለት በወጣው መረጀሰ ታጋቾችን ለማስለቀቅ እየተደረገ ያለው ድርድር ተስፋ ሰጪ እየሆነ መምጣቱ እና በቅርቡም የተወሰኑ ታጋቾችን ለማስለቀቅ ስምምነት ሊኖር ይችላል ተብሏል።
የኳታር ጠቅላይ ሚኒስትር በቅርቡ ታጋቾች የማስለቀቅ ስምምነት እንደሚደረስ ተስፋ እንዳላቸው ማሳወቃቸውን ተከትሎ፤ በአሜሪካ የእስራኤል አምባሳደር ማይክል ሄርዞግ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ታጋቾች በቀጣይ ቀናት ይለቀቃሉ ብለዋል።
በየጊዜው እየጨመረ የመጣው የሟቾች ቁጥር
እስራኤል በጋዛ እያካሄገችው ያልተቋረጠ የአየር ድብደባ ተከትሎ በጋዛ የሞቱ ፍሊስጤማውያን ቁጥር ከ13 ሺህ ማለፉን በሃማስ የሚመራው የጋዛ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። በእስራኤል የአየር ድብደባ ከሞቱ ፍሊስጤማውያን መካከል 8 ሺህ 300 ያህሉ ህጻናትና ሴቶች ናቸው።
በእስራኤል የሃማስጥን ጥቃት ተከትሊ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ1 ሺህ 400 ወደ 1 ሺህ 200 ዝቅ ያደረገች ሲሆን፣ 200 ሰዎች አሁንም በሃማስ እንደታገቱ ነው።