አሜሪካ በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጥፋተኛ የተባለ ዜጋዋን አፍና ገደለች
ግለሰቡ የሁለት ልጆች እናት የሆነች ሴትን አስገድዶ ከደፈረ በኋላ ገድሏታል ተብሏል
![](https://cdn.al-ain.com/images/2025/2/07/258-085237-e6971cfd-1fe2-4ff0-93b3-a2b5a60786a0-16x9-1200x676_700x400.jpeg)
የ14 ዓመት ታዳጊ በመድፈር ወንጀልም ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘው ይህ አሜሪካዊ በናይትሮጅን ጋዝ ታፍኖ እንዲሞት ተደርጓል
አሜሪካ በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጥፋተኛ የተባለ ዜጋዋን አፍና ገደለች።
የ52 ዓመቱ ድሜትሪስ ፍሬዘር አሜሪካዊ ሲሆን በአስገድዶ መድፈር እና ግድያ ወንጀሎች ጥፋተኛ ሆኖ ተገኝቷል።
ግለሰቡ በአላባማ በርሚንግሀም ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ፓውሊን ብራውን የተባለች የሁለት ልጆች እናትን በመኖሪያ ቤቷ ገብቶ አስገድዶ ከደፈረ በኋላ እንደገደላት ሮይተርስ ተብሏል።
እንዲሁም በሌላ ጊዜ የ14 ታዳጊ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል መፈጸሙ መረጋገጡን ተከትሎ በተደራራቢ ወንጀሎች ክስ ተመስርቶበት ነበር።
ይህንንም ተከትሎ ተከሳሽ ድሚትሪስ ፍሮዘር በሞት ፍርድ እንዲቀጣ የተላለፈበት ሲሆን የፍርድ ሂደቱ የተካሄደው የሞት ፍርድ የማይተላለፍበት ሚቺጋን ግዛት ውስጥ በመሆኑ ፍርዱ ወደ እድሜ ልክ እስራት ተቀይሮለት ነበር።
በአላባማ ወንጀል መፈጸሙ በፍርድ ቤት መረጋገጡን ተከትሎ ወደ አላባማ እስር ቤት ተላልፎ ሊሰጥ ችሏልም ተብሏል።
አላባማ ግዛት የሞት ፍርድ የተላለፈባቸው ፍርደኞችን አየር አጥሯቸው እንዲሞቱ የሚያደርግ ህግ ስላላት ይህም ወንጀለኛ በናይትሮጅን ጋዝ ታፍኖ ህይወቱ እንዲያልፍ መደረጉ ተገልጿል።
የመንግስታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሳይቀር የሚቃወመው የናይትሮጅን ጋዝ ግድያ በአሜሪካዋ አላባማ ብቻ ይፈጸማል።
ይህ የግድያ አይነት የሞት ፍርድ የተላለፈባቸው ሰዎች አየር አጥሯቸው በኦክስጅን እጥረት እንዲሞቱ የሚያደርግ ሲሆን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ተቆርቋሪዎች ግን ይህ አይነቱ የሞት ፍርድ ቅጣት ጭካኔ የተሞላበት ነው ሲሉ ይኮንኑታል።
የሞት ፍርድን የሚፈቅዱ ሌሎች የአሜሪካ ግዛቶችም ያሉ ሲሆን የአላባማ ናይትሮጅን ጋዝ ግድያ አሁን ለሶስተኛ ጊዜ ተፈጽሟል።
አሜሪካ ካሏት 50 ግዛቶች ውስጥ 23ቱ የሞት ፍርድን መፈጸም የሚያስችል ህግ ሲኖራቸው አቋርጠው የነበሩት አሪዞና፣ ኦሂዮ እና ተንሴ ግዛቶች ዳግም አስጀምረዋል።
ሀገሪቱ በተጠናቀቀው የፈረንጆቹ 2024 ዓመት ውስጥ ብቻ 25 ሰዎችን በሞት ቀጥታለች።