የቻይና እና ሩሲያ ወዳጅነት ያስደነገጣቸው ምዕራባውያን ለኬቭ 16 ቢሊዮን ዶላር ሊሰጡ ነው
ሩሲያ፤ቻይና በዩከሬን ጉዳይ የምትራምደው አቋም “ሚዛናዊ ነው”ብትልም ምእራባውያን በጥርጣሬ ይመለከቱታል
የወቅቱ የቻይናው መሪ የሞስኮ ጉብኝት በአሜሪካ እና አጋሮቿ ዘንድ ከፍተኛ ድንጋጤ የፈጠረ ነው ተብሏል
ገደብ የለሽ” ግንኙነት እንዲኖራቸው ከስምምነት የደረሱት የቻይና እና ሩሲያ መሪዎች ወዳጅነት ለምእራባውያን እጅግ አሳሳቢ ሆኖ እየመጣ ጉዳይ ሆኗል፡፡
በተለይም ከዩክሬን ጦርነት ጋር በተያያዘ ዓለም በሩሲያ ላይ ሲረባረብ ቻይና የምታራምደው የተለያ አቋም የቤጂንግ-ሞስኮ ግንኙነት እጅግ የጠበቀ መሆኑ የሚያመላክት እንደሆነ ይነሳል፡፡
ሩሲያ ፤ ቻይና በደም አፋሳሹ የዩክሬን ጦርነት ጉዳይ የምትራምደው አቋም ሚዛናዊ ነው ብላ ብታምንም አሜሪካና ምእራባውያን አጋሮቿ ነገሩን በጥርጣሬ እንደሚያዩት ሲግልጹ ይደመጣሉ፡፡
የወቅቱ የቻይናው መሪ የሞስኮ ገብኝት ያስደነገጣት አሜሪካ ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ እውነት ካላቸው በፑቲን ላይ ጫና በመፍጠር ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ በአውሮፓ ትልቁን ግጭት እንዲቆም ያድርጉ ስትልም ተደምጣለች፡፡
ፕሬዝዳንት ሺ የሩሲያው አቻቻው ፑቲን የዩክሬንን ሉዓላዊነት እንዲያከብሩ ሊነግርዋቸው ይገባልም ነበር ያለችው ዋሽንግተን፡፡
ነገር ግን የፕሬዝዳቱ የሁለት ቀን የሞስኮ ቆይታ አሜሪካ እና አጋረቿ እንዳሰቡት ሳይሆን መሪዎቹ የሁለትየሽ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር የመከሩበት ጥሩ አጋጣሚ ሆኖ ማለፉ እየተነገረ ነው፡፡
መሪዎቹ ዋሽንግተን ለዓለም ሰላም ጠነቅ እየሆነች መምጣቷን እንዲሁም አሁን ላይ ኔቶን ሽፋን በማድረግ ወደ እስያ-ፓሲፊክ ቀጠና ለመግባት እየሞከረች መሆኗ በተመለከተም መምከራቸውም ባወጡት የጋራ መግለጫ አስታውቀዋል፡፡
በተለይም የቻይናው ፕሬዝዳንት የሞስኮ አቻቸው ቭላድሚር ፑቲንን አሞካሹ የሚለውን ዜና መሰማቱ ምእራባውያንን የስደነገጠ ሆኗል፡፡
ጉብኝቱ መፍትሄ የሚያመጣ ሳይሆን ለአንድ ዓመት የዘለቀውን ደም አፋሳሹን የዩክሬን ጦርነት የሚያበረታታ ነው ሲሉም ተችተውታል፡፡
በዚህም የቻይና እና ሩሲያ ወዳጅነት ያስበረገጋቸው ምእራባውን ለኪቭ ተጨማሪ ገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ወስነዋል፡፡
ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ.ኤም.ኤፍ) በጦርነት ለተጎዳችው ኪቭ ለአራት አመታት የሚቆይ የ15.6 ቢሊዮን ዶላር የብድር ፓኬጅ ለማመቻቸት ቅድመ ስምምነት መደረጉን አስታውቋል።
ገንዘቡ ለአንድ ዓመት በዘለቀው ጦርነት በሩሲያ ኃይሎች መሰረተ ልማቶቿ እና በኢኮኖሚዋ ላይ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባትን ዩክሬን ለማገዝ ያለመ ነው ተብሏል፡፡
ምእራባውያን ዩክሬንን መደገፋቸው አጠናክረው ቢቀጥሉበትም የሩሲያው ፕሬዝዳንት ምዕራባውያን ለኪቭ የሚያደርጉት ገንዘብም ሆነ ጠር መሳሪያ ድጋፍ ጦርነቱንከማባበስና የዜጎችን ሰቆቃ ከማራዘም በዘለለ ምንም ፋይዳ እንደሌለው ተናግረዋል፡፡
ፑቲን ከሺ ጋር ባደረጉት ስብሰባ በኋላ በሰጡት አስተያየት፤ ብሪታኒያ ዩራኒየም የያዙ ታንክ ጥይቶችን ወደ ዩክሬን ለመላክ ማቀዷን አውግዘዋል፣ ውጤቱንም የከፋ እንደሚሆንም አስጠንቅቀዋል።
"ይህ ሁሉ የሚሆን ከሆነ ሩሲያዊያን ምላሽ መስጠት አለባቸው፤ ምክንያቱም ምዕራባውያን በጋራ ሆነው የኒውክሌር ቁሳቁስ ያላቸውን የጦር መሳሪያዎች መጠቀም ጀምረዋል" ብለዋል የሞስኮው ኃያል ሰው ፑቲን፡፡