በድንበሩ ግጭት ጉዳይ መግለጫ የሰጡት የሱዳን ጦር ቃልአቀባይ ከኃላፊነት ተነሱ
የቃልአቀባዩ ከስልጣን መነሳት ሰሞኑን ከሰጡት መግለጫ ጋር ይያያዝ ወይንም አይያያዝ የታወቀ ነገር የለም
በኢትዮ-ሱዳን ድንበር ግጭት ጉዳይ መግለጫ የሰጡት የሱዳን ጦር ቃልአቀባይ አሚን መሀመድ ሐሰን(ዶ/ር) ከኃላፊነት ተነሱ
በኢትዮ-ሱዳን ድንበር ግጭት ጉዳይ መግለጫ የሰጡት የሱዳን ጦር ቃልአቀባይ አሚን መሀመድ ሐሰን(ዶ/ር) ከኃላፊነት ተነሱ
የሱዳን ጦር ቃል አቀባይ አሚን መሀመድ ሐሰን(ዶ/ር) ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን የተለያዩ የሱዳን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡
ቃል አቀባዩ ለመገናኛ ብዙሃኑ በላኩት መልእክት በስራቸው ላይ በነበሩበት ወቅት ሚዲያዎች አደረጉልኝ ላሉት ድጋፍ አመስግነዋቸዋል፡፡ ከኃላፊነት መነሳታቸውም የወታደራዊ ስራ ባህሪይ መሆኑን የገለጹት ቃልአቀባዩ “ሁሌም መቀያየር ያለ ነው” ብለዋል፡፡
ከኃላፊነት የተነሱት ቃል አቀባይ “ማንም ሙሉ ሰው የለም፤ ፈጣሪ ብቻ ነው ሙሉ” የሚል መልእክትም አስተላልፈዋል፡፡
ቃል አቀባዩ አሚን መሀመድ ሐሰን(ዶ/ር) ሰሞኑን በኢትዮጵያናሱዳን ድንበር አዋሳኝ አካባቢ ተከስቶ የነበረውን ግጭት አስመልክቶ ተከታታይ መግለጫ ሲሰጡ ነበር፡፡ ቃል አቀባዩ ሰጥተውት በነበረው መግለጫ “የኢትዮጵያ ታጣቂዎች” በመከላከያ በመታገዝ በሱዳን ወታደሮችና በሱዳን ዜጎች ላይ ጥቃት አድርሰዋል የሚል ክስ በከፍተኛ ድምጸት በሀገሪቱ ሚዲያዎች በኩል መግለጫ ሲሰጡ ነበር፡፡
የቃልአቀባዩ ከስልጣን መነሳት ሰሞኑን ከሰጡት መግለጫ ጋር ይያያዝ ወይንም አይያያዝ የታወቀ ነገር የለም፡፡
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በበኩል ሁለቱን ሀገራት ወደ ግጭት የሚወስድ ምንም ምክንያት እንደሌላ ገልጾ፣ በግጭቱ በሁለቱም በኩል ህይወታቸውን ላጡ ዜጎች ማዘኑን በትናንትናው እለት ገልጿል፡፡
አሁን ላይ የሁለቱም ሀገራት ህዝቦች ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴያቸውም መመለሳቸውንም ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡
ሱዳን ኢትዮጵያና 1600 ኪ.ሜ የሚረዝም የየብስ ድንበር ይጋራሉ፤ በመካከላቸው ያለው ድንበር መሬት ላይ ተለክቶ አልተካለለም፡፡