የአልጀሪያ ህገመንግስት ሀገሪቱ ነጻነቷን ካገኘች በኋላ ለ8ኛ ጊዜ ተሻሽሏል
የአልጀሪያ ህገመንግስት ሀገሪቱ ነጻነቷን ካገኘች በኋላ ለ8ኛ ጊዜ ተሻሽሏል
የአልጀሪያ ኢንዲፔንደንት ብሄራዊ የምርጫ ባለስልጣን ኃላፊ ሞሃመድ ቻርፊ እንዳስታወቁት በህዝበ ውሳኔ የተመረጠው የህገመንግስት ማሻሻያ በ66በመቶ ምጥነት ድምጽ ጸድቋል፡፡
ቻፊ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ መምረጥ ከሚችሉት 24.4 ሚሊዮን ህዝብ ውስጥ 5.6 ሚሊዮን መራጮች ተሳትፈዋል፤ በዚህም የተሳተፉት 23.7 በመቶ ነው ተብሏል፡፡
ኃላፊው እንደገለጹት እንዲጸድቅ በአዎንታ ድምጽ የሰጡት 3.3 ሚሊዮን ወይም 66.8 በመቶ ናቸው ብለዋል፡፡
ቻርፊ የህዝበ ውሳኔው ውጤት ከህግና ከህገመንግስት አንጻር ሲታይ ትክክል መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ኃላፊው እንደገለጹት ህዝበ ውሳኔው ላይ የታየው ተሳትፎ አዲስ አልጀሪያን ለመገንባት የሚያስችል የህዝብ ድጋፍ መኖሩን ነው፤ ህዝብ የራሱን ሀሳብ ማስቀመጥ ነበረበረት፤በቅዳሜ ህዝበ ውሳኔ ያሳየው ይሄንኑ ነው፡፡
የአልጀሪያ ህገመንግስት ሀገሪቱ ነጻነቷን ካገኘች ከፈረንጆቹ 1962 ወዲህ ለ8ኛ ጊዜ ተሻሽሏል፡፡
አዲሱ የጸቀው ህገመንግስት የተባበሩት መንግስታት ሰለም አስከባሪን ለመርዳት ወደ ውጭ ወታደር ልትልክ ትችላለች የሚል አወዛጋቢ አንቀጽ ተካቶበታል፡፡