በታንዛኒያ የተካሄደውን ምርጫ ውጤት ያልተቀበሉት የዋና ተቃዋሚ መሪ ቱንዱ ታሰሩ
በታንዛኒያ የተካሄደውን ምርጫ ውጤት ያልተቀበሉት የዋና ተቃዋሚ መሪ ቱንዱ ታሰሩ
የታንዛኒያ ፖሊስ የዋና ተቃዋሚ ፓርቲ (ቻደማ) መሪ የሆኑትን ፍሪማን ምቦየን ማሰሩን በባለፈው ሳምንት ምርጫ የፓርቲው እጩ የሆኑት ቱንዱ ሊሱ አስታውቀዋል፡፡
ተቃዋሚዎች ምርጫው መጠነ ሰፊ ማጭበርበር ታይቶበታል በማለት ምርጫው እንዲደገም፤ ፕሬዘዳንት ማጉፉሊ 84 በመቶ በማግኘት በድጋሚ ወደ ስልጣን ያመጣውን የምርጫ ውጤት ለመቃወም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ከፓርቲው መሪ ምቦየ ጋር የቀድሞው የፓርላማ አባል ጎድ ብለስ ለማ፣ የቀድሞ የዳሬ ሰላም ከንቲባ ኢሳያ ምዊታ፣የቀድሞው የኡብንጎ ማዘጋጃ ቤት ኃላፊ ቦኒፌስ ጃኮብ ታስረዋል፡፡
ሊሱ ሊያዙ እንደሆነ እኩለ ሌሊት ላይ መልእክት ማግኘታቸውን ለሮይተርስ ተናግረዋል፡፡
በስዋህሊ ቋንቋ የሚታተመው ምዋንቺ የተባለው እለታዊ ጋዜጣ የዳሬሰላምን ፖሊስ ኮማንደር ላዛሮ ማምቦሳሳ ምቦየንና ሌሎች ተቃዋሚዎች እንደታሰሩ መናገራቸውን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡
አሜሪካ በዴሞክራሲያዊ ሂደት ላይ ስልታዊ ጣልቃገብነት እየተካሄደ መሆኑ እንደሚያሳስባት ስትገልጽ ዩናይትድ ኪንግደም በበኩሏ የፖሊስ የኃይል እርምጃና የጸጥታ መደፍረስ ሪፖርት እንስጨነቃት ገልጻለች፡፡