የአልጀሪያ መንግስት ማክ የተባለውንና በሀገሪቱ በአሸባሪነት የተፈረጀውን ተገንጣይ ቡድን ሞሮኮ ትረዳላች ሲል ክስ አቅርቧል
የአልጀሪያ ከፍተኛ ካውንስል በትናንትናው እለት በአልጀሪ የአየር ክልል ሁሉም የሞሮኮ የሲቪልና የወታደራዊ አውሮፕላን በረራዎች እንዳያልፉ ውሳኔ ማሳለፉን የአልጀሪያ ፕሬዘዳንት ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡
ይህ ወሳኔ የተላለፈው አልጀሪያ ከሞሮኮ ጋር ያላትን ግንኙነት ካቋረጠች ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
- ከእስራኤል አቻው ጋር አልወዳደርም ያለው አልጀሪያዊው የጁዶ ስፖርተኛ ለ10 ዓመት ታገደ
- ለአልጀርሱ ስምምነት መፈረም አስተዋጽኦ ያደረጉት የቀድሞው የአልጀሪያ ፕሬዝዳንት አረፉ
ጽ/ቤቱ እንደገለጸው እገዳው በሞሮኮ የተመዘገቡ የአውሮፕላኖችን ሁሉ ያካትታል፡፡ በዘህ ጉዳይ ላይ ከሞሮኮ በኩል መልስ አለመሰጠቱን የዘፈበው ሮይተርስ ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበው ከሆነ እገዳው ሞሮኮን ከቱኒዚያና ቱርክ ጋር የሚያገናኙ በሳምንት የሚካሄዱ 15 በረራዎችን ያስተጓጉላል፡፡
የአልጀሪያ እርምጃ ያን ያህል ጉዳት እንደማጥኖረውና በሜዲትራኒያን በኩል አቅጣጫ በመቀየር መንቀሳቀስ ይቻላል ተብሏል፡፡ የሞሮኮ አየር መንገድም በአልጀሪያ ወሳኔ ላይ እስካሁን መልስ አልመስጠቱ ተጠቅሷል፡፡
አልጀሪያ ከሞሮኮ ጋር ያላትን የዲፕሎማሲ ግንኙነት ያቋረጠችው፤ ብዙ ህዝብ ያላት ጉረቤቷ ሞሮኮ ያሳየቸው ጸብ አጫሩ ድርጊት የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ለአስርት አመታት መጉዳቱን ተከትሎ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
የአልጀሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ራምዳኔ ላማምራ ሞሮኮ፣ የአልጀሪያን ባለስልጣናት ለመሰለል ፔጋሱስ ስፓይዌር ተጠቅማለች እንዲሁም ተገንጣይ ቡድኖችንና ደግፋለች ስትል ከሳለች፡፡ የሞሮኮ መንግስት በአልጀሪያ ላይ የሚያራምደውን ጸብ አጫሪ ድርጊት ማቆም እንደማይችል የገለጹት ሚኒስትሩ ግንኙነቱ በአስቸኳይ እንዲቆም አዘዋል፡፡
የአልጀሪያ መንግስት ማክ የተባለውና በሀገሪቱ በአሸባሪነት የተፈረጀውን ተገንጣይ ቡድን ሞሮኮ ትረዳላች ሲል ክስ አቅርቧል፡፡ ማክ በአልጀሪያ ተከስቶ ለነበረው እሳትና የ65 ሰዎችን ሂወት ለቀጠፈው የእሳት አደጋ ተጠያቂ አልጀሪያ አድርጋዋለች፡፡