በሀገሪቱ ያለው የስራ አጥነት መጠንም ቢሆን 12 በመቶ መድረሱ የዓለም ባንክ መረጃዎች ይጠቁማሉ
አልጄሪያ አይመን ቢን አብዱራህማንን አዲሱ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር በማድረግ ሾመች።
በከፍተኛ የኢኮኖሚ ቀወስ ውስጥ እንደተዘፈቀች የሚነገርላት ሰሜን አፍሪካዊቷ አልጄሪያ፤ ጠቅላይ ሚኒሰትር በማድረግ የሾመችው የቀድሞ ፋይናንስ ሚኒሰትሯ አይመን ቢን አብዱራህማንን ነው።
በትናንትናው ዕለት በሀገሪቱ ፓርላማ የተመረጡት አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አይመን በሀገሪቱ የተንሰራፋውን የኢኮኖሚ ቀውስ ይታደጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ነው የተገለጸው።
"አይመን ቢን አብዱራህማን ጠቅላይ ሚኒሰትር ሆነው ተመርጧል፤ በተቻለ ፍጥነት ከፖለቲካ ፓርቲዎች እና ሲቪል ማህበረሰብ ጋር በመመካከር መንግስት እንደሚመሰርቱም ይጠበቃል” ብሏል የሀገሪቱ ምክር ቤት ባወጣው መግለጫው።
የ60 ዓመቱ አይመን ቢን አብዱራህማን እ.ኤ.አ ከ2019 ወዲህ አልጀርያን ሲመሩ የነበሩቱንና ባለፈው ሳምንት የስልጣን መልቀቅያ ያቀረቡትን ዓብደላዚዝ ድጅራድን የሚተኩ ይሆናል።
የድጅራድን መንግስት በሀገሪቱ የተጋረጠውን የኢኮኖሚ ቀውስ ፈተና ሆኖበት እንደቆየ የሚታወቅ ነው።
በሀገሪቱ ያለው የስራ አጥነት መጠንም ቢሆን 12 በመቶ መድረሱ የዓለም ባንክ መረጃዎች ይጦቁማሉ።
በቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የካቢኔ ስብስብ ደስተኛ ያልነበሩት ፕሬዝዳንት ዓብደልመጂድ ተቦብኔ ለተሰናባቹ ጠቅላይ ሚኒሰትር ያላቸው ምስጋና ገልጸዋል።
ተሰናባቹ ጠቅላይ ሚኒሰትር ዓብደላዚዝ ድጅራድን “በአስቸጋሪ የኮቪድ ወቅት” ለሰጡት አመራርም ፕሬዚዳንቱ አመስግነዋል።
ከ407 የሀገሪቱ ፓርላማ ወንበር 65ቱን በመያዝ ሶስተኛ ደረጃ የያዘው የአልጀርያ እስላማዊ ፓርቲ፤ የህብረተሰብ ንቅናቄ ለሰላም (ኤም.ኤስ.ፒ ) አዲሱን መንግስት እንደማይቀላቀል ከወዲሁ ግልጽ አድርጓል።
የሀገሪቱ ነባር ብሔራዊ ነፃነት ግንባር (ኤፍ.ኤን.ኤን) በሰኔ 12 በተካሄደው ድምጽ የመራጮችን ተሳትፎ 23 በመቶ ያገኘበትን ከፍተኛ መቀመጫ አግኝቷል።
የአልጄሪያ የረጅም ጊዜ ተፎካካሪ “ሂራክ” የዴሞክራሲ ደጋፊ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ምርጫውን አቋርጧል።
ይፋዊው ውጤት ከመድረሱ በፊት ለሙስሊም ወንድማማችነት ቅርበት ያለው መካከለኛ እስላማዊ ፓርቲ የሆነው ኤም.ኤስ.ፒ በአብዛኞቹ ክልሎች እጩዎቹ ግንባር ቀደም መሆናቸውን በመግለፅ የመንግስት አካል ሊሆን እንደሚችል ፍንጭ ሲሰጥ ቆይቷል።
የኤም.ኤስ.ፒ ኃላፊ አብደራዛክ ማክሪ በአልጄርስ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ “የታሰበው ነገር በፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ እድገቶች ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር አያስችለንም” ብለዋል።
ሥራ አስፈፃሚው አራት ወይም አምስት ሚኒስትሮችን የሚመርጥባቸውን የ27 ስሞች ዝርዝር እንዲያቀርብ ተጠይቆ እንደነበረም ገልጻል።
ይሁን እንጅ" ሚኒስትሮቻችንን (በመንግስት ውስጥ) የመምረጡ ጉዳይ የእኛ ጉዳይ አይደለም፤ ይህ ተቀባይነት የሌለው ነው" ያሉት ኃላፊው።
ማክሪ "እኛ ፊት ለፊት ሳይሆን በሥልጣን ላይ መሆን እንፈልጋለን" ሲሉም አክሏል።
ኤም.ኤስ.ፒ ከ 1996 እስከ 2011 ድረስ ተከታታይ የአልጄሪያ መንግስታት አካል እንደነበር ይታወቃል።