ፕሬዚዳንት ሆነው እንዴት የሚጠቀሙበት ንብረት ጠፋ የሚለው መነጋሪያ ሆኖ ቆይቷል
በኬፕታውን ጉብኝት ላይ የነበሩት የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎዛ አይፓድ እንደጠፋባቸው ገለጹ፡፡
ፕሬዚዳንቱ ለመገናኛ ብዙኃን ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት በተዘጋጁበት ወቅት አይፓዳቸው መጥፋቱን አስታውቀዋል።
የመነጋገሪያ ፖዲየሙ ላይ እንደወጡ “አይፓዴ ወዴት ጠፋ፤ ማን ወሰደው?” በሚል ሲጠይቁ ተስተውሏል፡፡ “በቃ ጠፋ ማለት ነው፤ በቃ የለም ማለት ነው“ በማለት ሲናገሩ ተስተውሏል፡፡
“በመጨረሻም በቃ አይፓዴን ሰረቁኝ ማለት ነው“ እያሉ ነበርም ተብሏል።
ፕሬዚዳንቱም “ሁልጊዜ የምንጠቀምበትን ነገር በሰው ማስያዝ እኮ ችግሩ ይህ ነው” ማለታቸውንም የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
በመጨረሻም አይፓዱ መገኘቱ የተገለጸ ሲሆን የፕሬዚዳንቱ ጽህፈት ቤት የአይፓዱን መጥፋት አስተባብሎ ነበር ተብሏል።
ይሁንና ሳውዝ አፍሪካ ፕሬዚዴንሲ በሚል ይፋዊ የትዊተር ገጽ ላይ የተጻፈ መልዕክት እንደሚያሳየው የፕሬዚዳንቱ አይፓድ ጠፍቶ ነበር።