የዘንድሮው አውሮፓ ዋንጫ በጀርመን አዘጋጅነት ከሁለት ሳምንት በኋላ ይጀመራል
ዴቪድ ቤካም የቻይናው አሊ ኤክስፕረስ ኩባንያ አምባሳደር ሆኖ ተሾመ፡፡
እንግሊዛዊው ኮኮብ ዴቪድ ቤካም የቻይናው አሊ ኤክስፕረስ ኩባንያ አምባሳደር ተደርጎ ተሾሟል፡፡
በቻይናዊው ቢሊየነር ጃክማ ባለቤትነት የተያዘው አሊ ባባ ኩባንያ በስሩ ካሉት ድርጅቶች መካከል አሊ ኤክስፕረስ አንዱ ነው፡፡
ይህ የሎጅስቲክስ ኩባንያ ከሁለት ሳምንት በኋላ በጀርመን የሚጀመረው የአውሮፓ ዋንጫ እግር ኳስ ውድድርን ስፖንሰር ሆኗል፡፡
የቀድሞው ማንችስተር ዩናይትድ፣ ሪያል ማድሪድ እንዲሁም የእንግሊዝ እግር ኳስ ተጫዋች የሆነው ዴቪድ ቤካም አሊ ኤክስፕረስን በአውሮፓ ዋንጫ ጎን ለጎን ለማስተዋወቅ ተስማምቷል፡፡
እንደ ቢቢሲ ዘገባ ከሆነ ዴቪድ ቤካም አሊ አክስፕረስን ለማስተዋወቅ ምን ህል ገንዘብ እንደተከፈለው ይፋ አልተደረገም፡፡
ብሪታንያ የኢትዮጵያ አበባ ያለ ግብር ወደ ሀገሯ እንዲገባ ፈቀደች
የዘንድሮው የአውሮፓ ዋንጫ በጀርመን አስተናጋጅነት ከሰኔ 7 ቀን እስከ ሐምሌ 7 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚካሄድ ይጠበቃል፡፡
በአሜሪካ ሜጀር ሊግ በሚወዳደረው ሚያሚ እግር ኳስ ክለብ ባለቤት የሆነው ዴቪድ ቤካም 580 ሚሊዮን ዶላር ሀብት ባለቤትም ነው፡፡
አሊ ኤክስፕረስ ከኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ አምራቹ ቢዋይዲ እና ቪቮ በመቀጠል የአውሮፓ ዋንጫን ስፖንሰር ያደረገ ሶስተኛው የቻይና ኩባንያ ሆኗል፡፡