የብሪታኒያ የደህንነት ኃላፊ በሳይበር ምህዳር ቀጣዩ ጥቂት ዓመታት በጣም አደገኛ ይሆናል ብለዋል
ብሪታኒያ ቻይና ትልቅ እና አደገኛ የሳይበር ደህንነት ስጋት ደቅናብኛለች ስትል ከሰሰች።
የብሪታኒያ የደህንት ቢሮ ኃላፊ አኔ ክሰት-በትለር እንደተናገሩት ከሆነ፤ በሀገሪቱ ላይ ቻይና፣ ኢራን እና ሩሲያ የሳይበር ደገህንነት ስጋትን ደቅነዋል ብለዋል።
ኃላፊዋ አክለውም ከሩሲያ እና ከኢራን የተደቀኑ የሳይበር ጥቃቶች ጊዜያዊ ቢሆኑም የቻይና ግን ለዘመናት ፈተና ሆና ልትቀጥል ትችላለች ሲሉ ገልጸዋል።
የብሪታኒያ የደህንት ቢሮ ኃላፊ አኔ ክሰት በትለር በበርኒንግሃም በተካሄደ የደህንነት ጉባዔ ላይ ባደረጉት ንግግርም፤ “ቀጣይ ጥቂት ዓመታት በጣም አደገኛ እና የሽግግር ጊዜ ይሆናል” ብለዋል።
ኃላፊዋ አኔ ክሰት-በትለር በንግግራቸውም፤ ከሩሲያ በኩል የተደቀነው የሳይበር ጥቃት አጣዳፊ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የተስፋፋ ነው ያሉ ሲሆን፤ ኢራን በሳይበር ምህዳር ላይ ጠበኛ ሆና ቆይታለች ብለዋል።
ሆኖም ግን በጣም ከባዱ እና አስቸጋሪው ስጋት ከቻይና በኩል ነው የተደቀነው ሲሉም ተናግረዋል።
"በሳይበር ምህዳር ውስጥ ኃላፊነት የጎደለው የቻይና ድርጊት ሁሉንም የበይነመረብ ደህንነትን ለአገዳ ያጋለጠ ነው ብለን እናምናለን" ብለዋል የብሪታኒያ የደህንት ቢሮ ኃላፊ አኔ ክሰት በትለር ።
ቻይና ዓለም አቀፉን የቴክኖሎጂ ስታንዳርድ ለራሷ እንዲመች አድርጋ መቀየር ትፈላጋለች ያሉት ኃላፊዋ፤ በቀጣይ 10 እና 15 ዓመታት ውስጥም በሳይበር ምህዳሩ የበላይነትን ለመቀዳጀት እየሰራች ነው ብለዋል።
ብሪታኒያ በአሁኑ ወቅት ከባለ አምስት አይን የስለላ ተቋማት አጋሮቿ ጋር እየሰራች መሆኗን እና አጋሮቿም አሜሪካ፣ ካናዳ፣ አውስትራሊያ እና ኒውዚላንድ መሆናቸውን አስታውቃል።