የቻይናው አሊባባ ኩባንያ ከዲፕ ሲክ የተሻለ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ይፋ አደረገ
ዲፕሲክ የተሰኘው የቻይናው ኤአይ ከሰሞኑ የአሜሪካ የቴክኖሎጂ ኩባያዎችን ማስደንገጡ ይታወሳል
መሰረታቸውን ቻይና ያደረጉ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የዓለም አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ውድድሩን እያፋጠኑት ይገኛሉ
የቻይናው አሊባባ ኩባንያ ከዲፕ ሲክ የተሻለ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ይፋ አደረገ፡፡
ከሰሞኑ መሰረቱን ቻይና ያደረገ አንድ ጀማሪ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ዲፕሲክ የተሰኘ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መተግበሪያውን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡
በ6 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የተሰራው ይህ መተግበሪያ ቢሊዮን ዶላሮችን ወጪ ያደረጉ እንደ ጎግል፣ ሜታ እና ኦፕን አይ ኩባንያዎችን አስደንግጧል፡፡
አሁን ደግሞ ሌላኛው የቻይናው የቴክኖሎጂ እና ሎጅስቲክስ ኩባንያ የሆነው አሊባባ ከዲፕሲክ የተሻለ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂውን ይፋ አድርጓል፡፡
ኪዌን 2.5 የተሰኘው ይህ ኤአይ የቻይናውን ሉናር አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ለተጠቃሚዎቹ ይፋ ማድረጉን አስታውቋል፡፡
የአሜሪካ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ያስደነገጠው ዲፕሲክ ማን ነው?
ኩባንያው በዋናነት ቴክኖሎጂውን ያስተዋወቀው የዓለም ኤአይ ቴክኖሎጂን ለመፎካከር እና በቻይና ቀዳሚ ተመራጭ ለመሆን አስቦ መሆኑን አስታውቋል፡፡
ኪዌን 2.5 የተሰኘው ይህ ኤአይ ከቻት ጅፒቲ እና ሌሎች ኤአይ ቴክኖሎጂዎች የተሸለ አገልግሎት እንደሚሰጥም አሊባባ ኩባንያ ገልጿል፡፡
የተለያዩ ሀገራት ኩባንያዎች የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የበላይነት ለመያዝ ፉክክር ላይ ሲሆኑ ባለሙያዎች በበኩላቸው ቴክኖሎጂው የከፋ አደጋ ከማድረሱ በፊት ቁጥጥር ሊደረግበት እንደሚገባ በማሳሰብ ላይ ናቸው፡፡