ካገለሉ ዲፕሎማቶች መካከል በአሜሪካ ውጪ ጉዳይ ሚንስቴር ውስጥ ከ20 ዓመት በላይ ያገለገሉ እንዳሉበትም ተገልጿል
የአሜሪካ ነባር ዲፕሎማቶች ራሳቸውን እያገለሉ ነው ተባለ።
ከሁለት ወር በፊት በተካሄደው የአሜሪካው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ያሸነፉት ዶናልድ ትራምፕ ዛሬ በይፋ ስልጣን ይረከባሉ።
47ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የሆኑት ትራምፕ ስልጣን መረከቢያቸው ጥቂት ሰዓታት ሲቀሩት በርካታ ዲፕሎማቶች ስራቸውን እየለቀቁ ነው ተብሏል።
ዋሽንግተን ፖስት እንደዘገበው ከሆነ ዶናልድ ትራምፕ በተሰናባቹ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳድር ስር ለህግ እና መርህ የማይከተሉ ወይም "ዲፕ ስቴት" የሚባል መዋቅር አለ ብለው ያምናሉ።
ይህን ለህግ እና መርህ አይገዛም ያሉትን ሀይል ለማጥፋት በውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ስር ያሉ ዲፕሎማቶች ራሳቸውን ከሀላፊነት እንዲያገሉ ጫና አድርገዋል ተብሏል።
እስካሁን ባለው ጊዜ ውስጥም ከ20 ዓመት በላይ በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ስር በዲፕሎማትነት የሰሩ እንዳሉም ተገልጿል።
በተለይም ከፍተኛ የሀላፊነት ቦታቆች ላይ ሲሰሩ የነበሩ ዲፕሎማቶች ከዛሬ ጀምሮ እንደማይፈለጉ ተነግሯቸዋልም ተብሏል።
ዶናልድ ትራምፕ ከ20 በላይ በሚሆኑ የሀላፊነት ቦታዎች ላይ ያመኑበትን ዲፕሎማት እንዲሾሙ ፈቃድ እንዳገኙም ተገልጿል።
ትራምፕ የቀድሞ ዲፕሎማቶችን በሀላፊነት የማያስቀጥሉት አሜቲካ ትቅደም ፖሊሲያቸውን አያስፈጽሙም በሚል ስጋት ምክንያት ነው ተብሏል።
ወደ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ይመለሳሉ ተብለው ከሚጠበቁት መካከልም ሊሳ ኬና የሚባሉት የቀድሞው ሚንስትር ማይክ ፖምፒዮ ፖለቲካ አማካሪ ወነኛዋ ናቸው።
ሴናተር ማርክ ሩቢዮ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ተደርገው እንዲሾሙ በትራምፕ በእጩነት የተያዙ ሰው ሲሆኑ ሹመታቸው በሀገሪቱ ህግ አውጪ ምክር ቤት እንደሚጸድቅ ይጠበቃል።