ተስፋ የተጣለበት የአልዛይመር መድሃኒት ከጥቁሮች ይልቅ ለነጮች የተሻለ እንደሚሰራ ተገለጸ
በሌሎች ምክንያት በሽታው ከተባባሰባቸው ጥቁር አሜሪካውያን ይልቅ ለነጮች እንደሚጠቅም እውቅ የአልዛይመር ተመራማሪዎች ተናግረዋል
ህክምናው የሚሰጠው ቤታ አሚሎይድ የተባለውን መርዛማ ፕሮቲን ከአእምሮ እንዲወገድ በማድረግ መሆኑን ተመራማሪዎቹ ተናግረዋል
ተስፋ የተጣለበት የአልዛይመር መድሃኒት ከጥቁሮች ይልቅ ለነጮቾ የተሻለ እንደሚሰራ ተገለጸ።
በምርምር ሂደት ውስጥ ያለው እና ተስፋ የተጣለበት የአልዛይመር (የመርሳት በሽታ) መድሃኒት ከጥቁሮች ይልቅ ነጮችን እንደሚጠቅም ተመራማሪዎች ገለጸዋል።
ቤታ አሚሎይድ የተባለውን መርዛማ ፕሮቲን ከአእምሮ እንዲወገድ በማድረግ የሚካሄደው አዲስ ህክምና በሌሎች ምክንያት በሽታው ከተባባሰባቸው ጥቁር አሜሪካውያን ይልቅ ለነጮች እንደሚጠቅም እውቅ የአልዛይመር ተመራማሪዎች ተናግረዋል።
አጋር ከሆኑት የባዮቴክ ኩባንያዎቹ ኢሳይ እና ባዮጅን የተገኘው ለቀምቢ መድሃኒት እና ኢሊ ሊሊይ እና ዶናኔንምባ በላብራቶሪያ ያበለጸጉት ህክም አልዛይመርን ለመቀነስ ትልቅ ተስፋ እንደተጣለበት ሮይተርስ ዘግቧል።
6.5 በመቶ የሚሆኑ አሜሪካውያን ከአልዛይመር ጋር ይኖራሉ። እነዚህ መድሃኒቶች የአልዛይመር በሽታ የሚስፋፋበትን ፍጥነት ይቀሳኑ ይላሉ ተመራማሪዎቹ።
ጥቁር አሜሪካውያን ላይ በተደረገው የላቦራቶሪ ምርመራ መድሃኒቱ ከጥቁሮች ይልቅ በነጮች ላይ የተሻለ ውጤታማ መሆኑን ጥናቱ አመልክቷል።
ጥናት ያደረጉት 10ሩ ተመራማሪዎች እንደገለጹት ከሆነ የበሽታው ምልክት የታየባቸው እና በጥናቱ ለመካተት ፍቃደኛ የሆኑ ጥቁር አሜሪካውያን በሙከራው በቂ አሚሎይድ ስለሌላቸው ለመኩራው ብቁ አለነበሩም ብሏል።
ነጮች ከሚጠቁበት መጠን በአንድ ከግማሽ የሚጠቁት ሂስፖኒክስ ባለቸው ዝቅተኛ የአሚሎይድ መጠን ምክንያት በጥናቱ አልተካተቱም። ነገረግን መጠኑ የጥቁሮችን ያህል ዝቅ እንደማይል ተመራማሪዎቹ ገልጸዋል።
የአልዛይመርን ባህሪ የሚወስነው የአሚሎይድ መጠን ልዩነትን የሚያሳዩ መረጃዎች መገኘታቸው በተመራማሪዎች ዘንድ አዲሱ ህክምና ማንነው የሚጠቅመዉ የሚል ጥያቄ አስነስቷል።
20 በመቶ የሚሆኑት ጥቁሮች ከነጮች አንጻር በሁለት እጥፍ በአልዛይመር የመጠቃት እድል ሲኖራቸው ከሂስፖኒክስ ደግሞ 14 በመቶ ያህል የመጠቃት እድል እንዳቸው ጥናቱ ይገልጻል።
ጥቂት የሚባሉ ተመራማሪዎች የአልዛይመር በሽታ በተለያየ የሰው ዘር ላይ የተለያየ ባህሪይ ያሳይ ይሆን ወይ የሚል ጥያቄም አጭሮባቸዋል።
ተመራሚሪዎቹ እንደሚሉት በቤታ አሚሎይድ መካከል ያለው ልዩነት አንዳንድ የጤና መለኪያዎች ለሁሉም የሰው ዘር አይሰሩም የሚለውን የሚያጠናክር ነው።
አሁን ላይ የአልዛይመር ተመራማሪዎች እንደ መርሳት የመሳሰሉትን ውጫዊ ምልክቶችን በመጠቀም የአልዛይመር በሽተኞችን ከመለየት ይልቅ በሰውነት ውስጥ የሚገኙ ከአልዛይመር ጋር ግንኙነት ያላቸውን ፕሮቲኖችን ወደመለየት እያመሩ ናቸው።
ተመራማሪዎቹ በዋናነት የሚያዩት በአእምሮ ውስጥ ያለውን ቤታ አሚሎይድን ነው።