ከሀገሪቱ ጦር ጋር እየተዋጉ እሚገኙት ጀነራል ሔመቲ ጦርነቱ እንዲቆም የሱዳን ጦር አዛዦች በሌላ ይተኩ ሲሉ ቅድመ ሁኔታ አስቀምጠዋል
ሱዳን የአየር ክልሏ ተዘግቶ የሚቆይበትን ጊዜ ወደ ነሀሴ 15 አራዘመች።
በፈረንጆቹ ሚያዝያ 15 የተጀመረው የሱዳን ጦርነት እንዲቆም በርካታ የተኩስ አቁም ስምምነቶች ቢፈረሙም ውጊያው አሁንም እንደቀጠለ ነው።
በሱዳን ብሔራዊ ጦር እና ፈጥኖ ደራሽ ሀይሎች መካከል እየተካሄደ ያለው ይህ ጦርነት በሪያድ፣ በአዲስ አበባ እና ካይሮ ውይይቶች ቢደረጉም ተፋላሚዎች ተኩስ ማቆም አልቻሉም።
- የሱዳን ጦር አመራሮች ከተቀየሩ በ72 ሰዓት ውስጥ የሰላም ስምምነት ለማድርግ ዝግጁ ነን- ሃሜቲ
- የሱዳን ጦር እና ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ሉዓላዊ ጽ/ቤቶችን ለመቆጣጠር እየተዋጉ ነው
በዚህ ጦርነት ምክንያት ከአምስት ሚሊዮን በላይ ሱዳናዊያን ከመኖሪያ መንደራቸው ተሰደዋል የተባለ ሲሆን 70 ሺህ ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ ሲሰደዱ ቀሪዎቹ ወደ ቻድ እና ግብጽ አምርተዋል ተብሏል።
ጦርነቱን ተከትሎ የሲቪል በረራዎች የታገዱ ሲሆን እገዳው እስከ ቀጣዩ ሁለት ሳምንታት ድረስ መራዘሙ ተገልጿል።
የሱዳን ተፋላሚ ወገኖች በጀነራል አልቡርሀን እና ጀነራል ሀምዳን ዳጋሎ በመመራት ላይ ሲሆን ሁለቱም ወገኖች እንደሚያሸንፉ በመናገር ላይ ናቸው።
የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሀይል አዛዥ የሆኑት ጀነራል ሀምዳን ዳጋሎ የሱዳን ጦር አዛዦች የሚቀየሩ ከሆነ በ72 ሰዓታት ውስጥ ውጊያ አቆማለሁ ሲሉ ተናግረዋል።
በሱዳን የተከሰተውን ጦርነት ለማስቆም የተለያዩ ጥረቶች በመካሄድ ላይ ሲሆኑ አሜሪካ፣ ሳውዲ አረቢያ፣ ኢጋድ እና ሌሎችም ወገኖች ያደረጉት ጥረት እስካሁም መፍትሔ አላስገኘም።