በተመድ የአሜሪካ አምባሳደር በድጋሚ ወደ አፍሪካ ሊመጡ ነው
አምባሳደር ሊንዳ ከዓለም ሁለተኛዋ ትልቅ አህጉር ከሆነችው አፍሪካ ጋር ለመተሳሰር የሚያቀኑ ሁለተኛዋ የካቢኔ አባል ናቸው
ባይደን የአሜሪካን ትኩረት በአህጉሪቱ ለማሳደግ ቁም ነገር እንዳላቸው ገልፀዋል
በተመድ የአሜሪካ አምባሳደር በድጋሚ አፍሪካን ሊጎበኙ ነው።
በተባበሩት መንግስታት የአሜሪካ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ-ግሪንፊልድ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ከአለም ሁለተኛዋ ትልቅ አህጉር ጋር ለመተሳሰር የሚያደርጉት ትልቅ ግፊት አካል በመሆን ወደ አፍሪካ የሚያቀኑ ሁለተኛው የካቢኔ አባል ናቸው።
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአሜሪካ ሚሲዮን እንዳስታወቀው አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ-ግሪንፊልድ ከፈረንጆቹ ጥር 25 ጀምሮ ወደ ጋና፣ ሞዛምቢክ እና ኬንያ ይጓዛሉ።
ጉዞው ከዋና ዋና የአሁን እና የቀድሞ የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት አባላት ጋር ያለን አጋርነት ለማረጋገጥ እና ለማጠናከር ያለመ መሆኑ ተነግሯል።
የቶማስ-ግሪንፊልድ ጉብኝት ባለፈው ሳምንት በግምጃ ቤት ፀሐፊ ጃኔት የለን የተደረገን 10 ቀናት የአፍሪካ ጉብኝት የተከተለ ነው።
ባይደን በታህሳስ ወር የአሜሪካ-አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ መገባደጃ ላይ በፈረንጆች 2023 ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ ሀገራትን እንደሚጎበኙ አሳውቀዋል።
የመሪዎች ጉባኤ እና ጉዞው አሜሪካ ከአፍሪካ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ ነው።
በአፍሪካ ቻይና በንግዱ አሜሪካን በበለጠችበት እና የጦር ኃይሏን ለመጨመር እየተንቀሳቀሰች ሲሆን፤ ሩሲያ ደግሞ ከማሊ እና ከመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ባለስልጣናት ጋር ወታደራዊ ግንኙነት አላት።
ኤቢሲ እንደዘገበው ባይደን በጉባዔው ላይ የአሜሪካን ትኩረት በአህጉሪቱ ለማሳደግ ቁም ነገር እንዳላቸው ገልፀዋል።
ለቀድሞዋ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር የአፍሪካ ረዳት ፀሀፊ ቶማስ-ግሪንፊልድ የመጀመርያው መዳረሻ ጋና ናት ተብሏል።
ከጥር 26 እስከ 27 በጉብኝታቸው ወቅት የአሜሪካ ሚሲዮን ከተመድ ባለስልጣናት፣ ስራ ፈጣሪዎች፣ ከአሜሪካ ልውውጥ የቀድሞ ተማሪዎች፣ የዓለም አቀፍ ግንኙነት ተማሪዎች እና አየር ንብረት ለውጥ ላይ ከሚሰሩ የሲቪል ማህበረሰብ አባላት ጋር እንደሚገናኙ ተገልጿል።
ከጥር 28 እስከ 29 የአምባሳደሯ የመጨረሻ ማረፊያ ኬንያ ስትሆን፤ በምክር ቤቱ የሁለት አመት የስራ ጊዜዋ ባለፈው ታህሳስ አብቅቷል።