“ተ.መ.ድ በሶማሊያ እየተስተዋለ ያለው አለመስማማት አሳስቦታል” -አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ-ግሪንፊልድ
የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሞሀመድ ፋርማጆ ስልጣናቸው ቢያበቃም እስካሁን አልተተኩም
የፀጥታው ም/ቤት የሶማሊያ መሪዎች ችግራቸውን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ ጥሪ አቅረበዋል
በሶማሊያ ሊካሄድ ከታቀደው አዲስ ምርጫ ጋር በተያያዘ እየተስተዋለ ያለውን አለመስማማት፤ የተባበሩት መንግሰታት የፀጥታው ም/ቤት እንደሚያሳስበው አንድ ከፍተኛ የተባበሩት መንግስታት ዲፕሎማት ገለጹ፡፡
የፕሬዝዳንት ሞሀመድ ሞሀመድ/ፎርማጆ/ የአራት አመታት የስልጣን ገደብ ባለፈው ወር ማብቃቱንና እሳቸውን የሚተካ መሪ አለመመረጡን የሚታወቅ ነው፡፡ ይሁን እንጂ አዳዲስ የሕግ አውጭዎች እስካሁን ካለመመራጣቸው ጋር ተያይዞ የምርጫው ሂደት እምዲዘገይ ምክንያት ሆነዋል ይላል የሮይተርስ ዘገባ፡፡
በዚህም በተባበሩት መንግስታት የአሜሪካ አምባሳደሯ ሊንዳ ቶማስ-ግሪንፊልድ 15 አባል ሀገራት በተሳተፉበት የም/ቤቱ ዝግ ስብሰባ “በሶማሊያ ፌዴራላዊ መንግስት እና በፌዴራል የክልል መንግስታት መሪዎች መካከል ስምምነት እንዲፈጠርና የተሻሻለው የምርጫ ሞዴል ተግባራዊ ለማድረግ ጥረቶች እየተደረጉ ናቸው” ብለዋል፡፡
አምባሳደሯ “የምክር ቤቱ አባል ሀገራት በሶማልያ እየታዩ ያሉ አለመስማማቶች ስጋት እንደፈጠሩባቸው በመግለፅ የሶማሊያ መሪዎች ካለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ገንቢ የሆነ ውይይት በማድረግ ያሉባቸው ያልተነሱ ጉዳዮችን እንዲፈቱ ጥሪ አቅርበዋል”ም ብለዋል አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ-ግሪንፊልድ፡፡