የሽግግር ምክርቤቱ ኃላፊ ጄነራል አብዱል ፋታህ አልቡርሃንና የፍትህ ሚኒስትሩ ከሱዳን ወደ ዩኤኢ በሚሄደው ቡድን ውስጥ ተካተዋል
የሽግግር ምክርቤቱ ኃላፊ ጄነራል አብዱል ፋታህ አልቡርሃንና የፍትህ ሚኒስትሩ ከሱዳን ወደ ዩኤኢ በሚሄደው ቡድን ውስጥ ተካተዋል
የሱዳን ባለስልጣናት እንዳስታወቁት ሀገራቸው ሽብርን ከሚረዱ ሀገራት ዝርዝር መዝገብ የምትሰረዝበትን መንገድ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በሚያደርጉት ጉዞ ከአሜሪካ ባለስልጣናት ጋር ይወያያሉ፡፡
የሱዳን የሽግግር መንግስት ሱዳንን ከዝርዝሩ ለማስጠፋት እየጣረ ሲሆን ይህም ሀገሪቱ የውጭ ብድር ልታገኝ የምትችልበትን እድል ያመቻችላታል ተብሏል፡፡
ባለፈው ነሀሴ ወር የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ ሱዳን ከእስራኤል ጋር ግንኙነት መጀመሯን በሱዳን ጉብኝት ባደረጉት ወቅት ገልጸው ነበር፡፡ የአሜሪካ ቁልፍ አጋር የሆነችው ዩኤኢና ባህሬን በአሜሪካ አማካኝነት በተካሄደው ድርድር ከእስራኤል ጋር ግንኙነታቸውን አድሰዋል፡፡ ዩኤኢ ለሩብ ምእተ አመት ያህል የነበረውን ነውር የሚመስል ነገር መስበር ችላለች፡፡
የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሌሎች የአረብ ሀገራት ከእስራኤል ጋር ወደ ስምምነት ይመጣሉ ብለው ተናግረዋል፡፡
ከእስራኤል ጋር የሚደረግ ግንኙነት እንደ ቀላል የማይታይና በተለይ በአልበሽር ጊዜ በነበሩ ሙስሊሞች ዘንድ አይወደደም፡፡
የሽግግር ምክርቤቱ ኃላፊ ጄነራል አብዱል ፋታህ አልቡርሃንና የፍትህ ሚኒስትሩ ናስረዲን አብደልባሪ ከሱዳን ወደ ዩኤኢ በሚሄደው ልኡካን ቡድን መካተታቸው ታውቋል፡፡ የልኡክ ቡድኑ መጀመሪያ ከዩኤኢ ባለስልጣናት ጋር ይገናኛል ተብሏል፡፡
ባለፈው የካቲት ወር የእስራኡሌ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ንታኒያሁና አል ቡርሃን በኡጋንዳ በገናኘታቸው በሱዳናውያን ተቃዋሚዎች ተወግዞ ነበር፡፡ ከዚያን ግዜ ጀምሮ ምንም እንኳን የእስራኤል ጄቶች በሰዱን የአየር ክልል ማለፍ ቢችሉም በእራኤልና ሱዳን ግንኙነት ማደስ ላይ ጥላ አጥሎቶ ነበር፡፡