በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የሞቱት ሰዎች ቁጥር በቻይና የሞቱትን ቁጥር በለጠ
በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የሞቱት ሰዎች ቁጥር በቻይና የሞቱትን ቁጥር በለጠ
በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ቻይና በቫይረሱ ምክንያት ያስመዘገበችውን የሞት ቁጥር መብለጡን የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲን ጠቅሶ የአሜሪካ ድምፅ ዘግቧል፡፡
በባልቲሞር የሚገኘው ዩኒቨርሲቲ እንደገለጸው በአሜሪካ እስካሁን 3,415 ሰዎች የሞቱ ሲሆን ይህም በቻይና ከሞቱት 3,309 ሰዎች የሚበልጥ ነው፡፡
ቫይረሱ ከፍተኛ የሞት ቁጥር ያስተናገደችው ጣሊያን በ12,428 ሞት አንደኛ ስትሆን ስፔን ደግሞ በ8,269 ሞት የሁለተኝነት ደረጃ ይዛለች፡፡ አሜሪካ በአንፃሩ በሞት ቁጥር ሶስተኛ ደረጃ መያዟን ዘገባው አስነብቧል፡፡
በአሁኑ ወቅት በአሜሪካ 175,067 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን በጣሊያንና በስፔንና ደግሞ እንደቅደም ተከተላቸው 105,792ና 94,417 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡
በቻይና ደግሞ 82,278 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡
ባለፈው ታህሳስ በቻይናዋ ውሀን ከተማ የተቀሰቀሰው ኮሮና ቫይረስ እስካሁን ድረስ 860,000 በላይ ህዝብ በመላው አለም ማጥቃቱን ጆንስሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ ያወጣው መረጃ ያሳያል፡፡ ቫይረሱ እስካሁን ከ42,0000 በላይ ለሆኑ ሰዎች ሞት ምክንያት ሆኗል፡፡