ውሻና ድመትን ጨምሮ 183 እንስሳቶችን በማቀዝቀዣ (ፍሪጅ) ውስጥ አድርቆ ያስቀመጠው አሜሪካዊ ታሰረ
ሚካኤል ፓትሪክ ቱርላንድ እንስሳቶችን ለምን ያደርቃቸው እንደነበር እስካሁን የታወቀ ነገር የለም
ግለሰቡ አንዳንዶቹን እንስሳቶች በህይወት እያሉ ወደ ማቀዝቀዣ አስገብቶ ያደርቃቸው እንደነበር አምኗል
የአሜሪካዋ አሪዞና ግዛት ፖሊስ በማዘቅዘዣው ውስጥ ውሻ፣ ድመት፣ ጥንቸሎች እና ወፎችን ጨምሮ 183 የደረቁ እንስሳትን አስቀምጦ የተገኘውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል።
በቁጥጥር ስር የዋላው ግለሰብ የ43 ዓመቱ ሚካኤል ፓትሪክ ቱርላንድ የተባለው የአሪዞና ነዋሪ ሰሆን፤ አድርቆ ካስቀመጣቸው እንስሳት አንዳንዶቹ በህይወት እያሉ ወደ ማዘቅዘዣው አስገብቶ ያደርቃቸው እንደነበር ለፖሊስ በሰጠው ቃላ አምኗል።
ግለሰቡ 94 ክሶች ቀርበውለታል ነው የተባለው።
የአሪዞና ፖሊስ ቃል አቀባይ ኣኒታ ሞርተንሰን “ስፍራው ላይ የተገኙ ምስሎች እጅግ የሚያስደነግጡና ልብ የሚነኩ” ናቸው ብለዋል።
“እኔ እንስሳትን በጣም ስለምወድ ምስሎቹን ሳይ በጣም ነው ያለቀስኩት” ያሉት ቃል አቀባይዋ፤ ፎቶግራፎችን ለሰው ለማሳየት እንኳን አልቻልኩም ሲሉ ተናግረዋል።
የአሪዞና ፖሊስ ባለስልጣናት፤ አሁን ላይ ሚካኤል ፓትሪክ ቱርላንድ የትዳር አጋር ብሪክሊን ቤክ ፍለጋ ላይ መሆናቸውንም አስታውቀዋል።
የአሪዞና ፖሊሶች ሚካኤል ፓትሪክ ቱርላንድን የፈጸመውን ወንጀል ለማወቅ የቻሉት ከጎረቤቶቹ በደረሳቸው ጥቆማ መሰረት እንደሆነ ገልጸዋል።
ሚካኤል ፓትሪክ ቱርላንድ እንስሳቶችን ለምን ፈሪጅ ላይ ያደርቃቸው እንደነበር እስካሁን የታወቀ ነገር የለም።