የአሜሪካ በሽታዎች ቁጥር ማዕከል ከኮሮና ታማሚዎች ሲሶ ያህሉ ምልክቶችን የማያሳዩ ናቸው ብሏል
ከኮሮና ታማሚዎች 35 በመቶ ያህሉ ምልክቶችን አያሳዩም-የአሜሪካ በሽታዎች ቁጥር ማዕከል
የአሜሪካ በሽታዎች መከላከልና ቁጥጥር ማዕከል (American CDC) ለሂሳብ አዋቂዎች እና ለህብረተሰብ ጤና መኮንኖች አዲስ መመሪያን አዘጋጅቷል፡፡
በመመሪያውም ከኮሮና ወረርሽኝ ሲሶ (አንድ ሶስተኛ) ያህሉ ምልክቶችን የማያሳዩ (asymptomatic) እንደሆኑ ግምቱን አስቀምጧል፡፡
http://https://www.cdc.gov/coronavirus/2019-ncov/hcp/planning-scenarios.html
“ምርጥ” በሚል ባስቀመጠው ግምትም ምልክቶችን ከሚሳዩ የቫይረሱ ታማሚዎች ዜሮ ነጥብ አራት በመቶ ያህሉ ይሞታሉ፡፡
65 እና ከዚያ በላይ ዕድሜ ካላቸው የቫይረሱ ታማሚዎች ደግሞ 1 ነጥብ 3 በመቶ ያህሉ ሟች ናቸው፡፡
49 ዓመት እና ከዚያ በታች ከሆኑት ደግሞ ዜሮ ነጥብ ዜሮ አምስት በመቶ ያህሉ ይሞታሉ፡፡
በምርጥ የቢሆን ግምቱም መመሪያው ምልክቱን ከሚያሳዩት 3 ነጥብ 4 በመቶ ያህሉ በሆስፒታሎች መታከም እንደሚያስፈልጋቸው ያመለክታል፡፡
ይህ መቶኛ 65 እና ከዚያ በላይ ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ላሉ ታማሚዎች ወደ 7 ነጥብ 4 በመቶ ከፍ የሚል ነው፡፡
እንደ ማዕከሉ ግምት ከሆነ የቫይረሱ 40 በመቶ ያህል ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈው አስተላላፊው ሰው ከመታመሙ በፊት ነው፡፡
ልክ ምልክቶቹን የሚያሳዩት ቫይረሱን እንደሚያስተላልፉም ሁሉ የማያሳዩትም ያስተላልፋሉ፡፡
ሆኖም አምስት ግምታዊ የቢሆን ሃሳቦችን (scenario) ያስቀመጠው ማዕከሉ አሃዛዊ መረጃዎቹ ሊደረስባቸው ከሚችሉ የቫይረሱ ነባራዊ እውነታዎች ጋር ሊቀየሩ እንደሚችሉ እና ለዕቅድ ዝግጅቶች ግብዓት እንዲሆኑ በማሰብ ብቻ መዘጋጀታቸውን አስታውቋል፡፡