በሩሲያ የፕሬስ የነጻነት ሁኔታ በእጅጉ እያሽቆለቆለ ነው ተብሏል
በእስር ላይ የሚገኘው አሜሪካዊ ጋዜጠኛ ኢቫን ጌርሽኮቪች በስለላ ክስ በሩሲያ ከታሰረ 100ኛ ቀኑን አስቆጥሯል።
የዎል ስትሪት ጆርናል ዘጋቢ እ.አ.አ. መጋቢት 29 በማዕከላዊ ሩሲያ የካተሪንበርግ ከተማ ለስራ በተጓዘበት ወቅት በቁጥጥር ስር ውሏል።
የሩሲያ ባለስልጣናት መቀመጫውን ሞስኮ ያደረገውን ጋዜጠኛ በስለላ ከሰዋል።
ቪኦኤ ጌርሽኮቪች፣ ዎል ስትሪት ጆርናል እና የአሜሪካ መንግስት የስለላ ክሱን አጥብቀው ክደዋል።
በፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ዘመን በሩሲያ የፕሬስ የነጻነት ሁኔታ እያሽቆለቆለ ባለበት ሁኔታ የጋዜጠኛው እስራት ዝቅተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን የመገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች ተናግረዋል።
የአሜሪካ ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ክሌይተን ዌይመርስ ለቪኦኤ እንደተናገሩት "የኢቫን መታሰር የፑቲንን የነጻ ፕሬስ ጦርነት እንደ አዲስ መባባስ አሳይቷል፤ ከሩሲያ የሀገር ውስጥ ሚዲያዎች ባለፈ ሙሉ በሙሉ ተዘግቷል" ብለዋል።
"ጋዜጠኛው የጋዜጠኝነትን ስራውን በመስራቱ ብቻ ለመቅጣት 100 ቀናት እስር ቤት መወርወር ረጅም ነው" ሲሉም አክለዋል።
ከቀዝቃዛው ጦርነት ማብቂያ በኋላ በሩሲያ ውስጥ በስለላ ወንጀል የተከሰሰው የመጀመሪያው አሜሪካዊ ዘጋቢ ጌርሽኮቪች ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ 20 ዓመታት በቅጣት ይጠብቀዋል።